ዔሳውም ዐይኑን አነሣና ሴቶችንና ልጆችን አየ፤ እንዲህም አለ፥ “እነዚህ ምኖችህ ናቸው?” እርሱም፥ “እግዚአብሔር ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለ።
መክብብ 6:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ ብዙ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም ብዙ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ እኔ ስለ እርሱ፥ “ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል” አልሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው መቶ ልጅ ሊኖረውና ብዙ ዓመት ሊኖር ይችላል፤ ምንም ያህል ይኑር፣ በሀብቱ ደስ ካልተሠኘበትና በአግባብ ካልተቀበረ፣ ከርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ነገር ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ፥ አንድ ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ ረጅም ዕድሜ አግኝቶ ብዙ ዘመን በሕይወት ቢኖርም፥ እንዲደሰትበት ከሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ድርሻውን ሳያገኝ ቀርቶ በመጨረሻም በክብር ለመቀበር ሳይበቃ ቢቀር፥ እኔ ስለ እርሱ አዝናለሁ፤ ከእንደዚህ ያለውም ሰው ይልቅ በእናቱ ማሕፀን ሞቶ የተወለደ ጭንጋፍ ይሻላል አልኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነፍሱም መልካምን ባትጠግብ መቃብርንም ባያገኝ፥ እኔ ስለ እርሱ፦ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ። |
ዔሳውም ዐይኑን አነሣና ሴቶችንና ልጆችን አየ፤ እንዲህም አለ፥ “እነዚህ ምኖችህ ናቸው?” እርሱም፥ “እግዚአብሔር ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለ።
ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፥ “በእንግድነት የኖርሁት የሕይወቴ ዘመንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕይወቴም ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ሆኑብኝ፤ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።”
ለአክአብም በሰማርያ ሰባ ልጆች ነበሩት፤ ኢዩም ደብዳቤ ጽፎ፥ የአክአብን ልጆች ለሚያሳድጉ፥ ለሰማርያ አለቆችና ሽማግሌዎች ወደ ሰማርያ ላከ።
እግዚአብሔርም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
ሮብዓምም ከሚስቶቹና ከቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን ወደደ፤ ዐሥራ ስምንትም ሚስቶችና ስድሳ ቁባቶች ነበሩት፤ ሃያ ስምንት ወንዶችና ስድሳ ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
ስለዚህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ልጅ አይኖርለትም፥ ሬሳውም በቀን ለትኩሳት፥ በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል።
በወደዱአቸውና በአመለኳቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጓቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም፥ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጓቸዋል፤ አያለቅሱላቸውም፤ አይቀብሯቸውምም፤ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።
የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር፤” አለ።