Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መክብብ 6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከፀ​ሐይ በታች ያየ​ሁት ክፉ ነገር አለ፥ እር​ሱም በሰው ላይ እጅግ የበዛ ነው።

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ሀብ​ት​ንና ጥሪ​ትን ክብ​ር​ንም ሰጠው፥ ከወ​ደ​ደ​ውም ሁሉ ለሰ​ው​ነቱ የከ​ለ​ከ​ላት የለም፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይበ​ላ​ዋል እንጂ ከእ​ርሱ ይበላ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላ​ሠ​ለ​ጠ​ነ​ውም፤ ይህም ከን​ቱና ክፉ ደዌ ነው።

3 ሰው መቶ ልጆች ቢወ​ልድ፥ ብዙ ዘመ​ንም በሕ​ይ​ወት ቢኖር፥ ዕድ​ሜ​ውም ብዙ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መል​ካ​ምን ባት​ጠ​ግብ፥ መቃ​ብ​ር​ንም ባያ​ገኝ፥ እኔ ስለ እርሱ፥ “ከእ​ርሱ ይልቅ ጭን​ጋፍ ይሻ​ላል” አልሁ።

4 በከ​ንቱ መጥ​ቶ​አል፥ በጨ​ለ​ማም ይሄ​ዳል፥ ስሙ በጨ​ለማ ይሸ​ፈ​ና​ልና።

5 ደግ​ሞም ፀሐ​ይን አላ​የም፥ አላ​ወ​ቀ​ምም፤ ስለ​ዚህ ከዚያ ይልቅ ለዚህ ዕረ​ፍት አለው።

6 ሺህ ዓመት ሁለት ጊዜ በሕ​ይ​ወት ቢኖር፥ መል​ካ​ም​ንም ባያይ፥ ሁሉ ወደ አንድ ስፍራ የሚ​ሄድ አይ​ደ​ለ​ምን?

7 የሰው ድካም ሁሉ በአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አት​ጠ​ግ​ብም።

8 ከአ​ላ​ዋቂ ይልቅ ለጠ​ቢብ ጥቅሙ ምን​ድር ነው? በሕ​ያ​ዋን ፊትስ መሄ​ድን ለሚ​ያ​ውቅ ለድሃ ጥቅሙ ምን​ድር ነው?

9 በዐ​ይን ማየት በነ​ፍስ ከመ​ቅ​በ​ዝ​በዝ ይሻ​ላል፥ ይህ ደግሞ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።

10 የሆ​ነው ሁሉ እነሆ፥ ስሙ አስ​ቀ​ድሞ ተጠራ፥ ሰውም እንደ ሆነ ታወቀ፤ ከእ​ር​ሱም ከሚ​በ​ረ​ታው ጋር ይፋ​ረድ ዘንድ አይ​ች​ልም።

11 ከን​ቱን የሚ​ያ​በዛ ብዙ ነገር አለና፥ ለሰው ጥቅሙ ምን​ድር ነው?

12 ሰው በከ​ንቱ ወራቱ ቍጥ​ርና እንደ ጥላ በሚ​ያ​ሳ​ል​ፈው ዘመኑ በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ለሰው የሚ​ሻ​ለ​ውን የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው? ወይስ ለሰው ከፀ​ሓይ በታች ከእ​ርሱ በኋላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ማን ይነ​ግ​ረ​ዋል?

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos