ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
ዘዳግም 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለራስህ ዕወቅ፤ ሰውነትህን ፈጽመህ ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ይህን ሁሉ ነገር አትርሳ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ከልቡናህ አይውጣ፤ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህም አስተምራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐይኖቻችሁ ያዩአቸውን ነገሮች እንዳትረሱ፣ ደግሞም በሕይወት እስካላችሁ ድረስ ከልባችሁ እንዳይጠፉ ብቻ ተጠንቀቁ፣ ነቅታችሁም ራሳችሁን ጠብቁ። እነዚህን ለልጆቻችሁና ከእነርሱ በኋላ ለሚወለዱት ልጆቻቸው አስተምሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን በዐይናችሁ ያያችሁትን ሁሉ እንዳትረሱና ከአእምሮአችሁ እንዳይጠፋ ተጠንቀቁ። ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር፦ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ፥ በምድርም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩ ዘንድ፥ ልጆቻቸውንም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን አሰማቸዋለሁ ብሎ በተናገረኝ ጊዜ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በኮሬብ በቆምህበት ቀን ዓይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይወድቅ ተጠንቀቅ፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አስታውቀው። |
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
በግብፃውያንም ላይ የተዘባበትሁትን ሁሉ፥ ያደረግሁባቸውንም ተአምራቴን በልጆቻችሁና በልጅ ልጆቻችሁ ጆሮች ትነግሩ ዘንድ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ራሳችሁን ጠብቁ፥ በሰንበትም ቀን ምንም ሸክም አትሸከሙ፤ በኢየሩሳሌምም በሮች አታግቡ፤
እንግዲህ እንዴት እንደምትሰሙ አስተውሉ፤ ላለው ይሰጠዋል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።”
“በምድር ላይ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ትወርሷት ዘንድ በሚሰጣችሁ ሀገር ታደርጉት ዘንድ የምትጠብቁት ሥርዐት፥ ፍርድም ይህ ነው።
የቦካውን እንጀራ ከእርሱ ጋር አትብላ፤ ከግብፅ ሀገር በችኮላ ስለ ወጣህ ከግብፅ ሀገር የወጣህበትን ቀን በዕድሜህ ሁሉ ታስብ ዘንድ የመከራን እንጀራ፥ ቂጣ እንጀራ ሰባት ቀን ከእርሱ ጋር ብላ።
መጽሐፉ ከእርሱ ጋር ይኑር፤ ዕድሜውንም ሁሉ ያንብበው። አምላኩን እግዚአብሔርን መፍራት ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ፥ ይህችንም ሥርዐት ጠብቆ ያደርግ ዘንድ፥
“ምስጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛና ለልጆቻችን ለዘለዓለም ነው።
አሁንም ይህችን መዝሙር ለእናንተ ጻፉ፤ ለእስራኤልም ልጆች አስተምሩአቸው፤ ይህችም መዝሙር በእስራኤል ላይ ምስክር ትሆንልኝ ዘንድ በአፋቸው አድርጓት።
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዝዙበት ዛሬ የምመሰክርላችሁን ቃል ሁሉ በልባችሁ አኑሩት።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስባቸው፤ እነርሱ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩና ለልጆቻቸውም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን ይስሙ ብሎኛልና በኮሬብ በተሰበሰባችሁ ጊዜ በፈጣሪያችሁ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ቆማችሁ ንገራቸው።
“እግዚአብሔር በኮሬብ ተራራ በእሳት መካከል ሆኖ በተናገራችሁ ቀን መልኩን ከቶ አላያችሁምና ሰውነታችሁን እጅግ ጠብቁ፤
ከእናንተ ጋር የተማማለውን የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የከለከለውን፥ በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ እንግዲህ ተጠንቀቁ።
እናንተ፥ ልጆቻችሁም፥ የልጅ ልጆቻችሁም በዕድሜአችሁ ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ፈርታችሁ እኔ ለእናንተ ያዘዝሁትን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ፥ ዕድሜአችሁም ይረዝም ዘንድ፤
“ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን፥ ሥርዐቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበረና የሰሙትም ለእኛ አጸኑት።
ኢያሱም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፥ “ልጆቻችሁ፦ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብለው በሚጠይቋችሁ ጊዜ፥
እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ። እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፤ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም።
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረጉ፤ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተው በዓሊምንና አስታሮትን አመለኩ።
የእስራኤልም ልጆች በዙሪያቸው ከነበሩት ከጠላቶቻቸው ሁሉ እጅ ያዳናቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን አላሰቡትም፤