እነዚያ ይስማኤላውያን ነጋዴዎችም ሲያልፉ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ ጐትተው አወጡት፤ ለይስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
ዘዳግም 33:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየወቅቱም ከምድሪቱ ምላት፥ በቍጥቋጦው ውስጥ ከነበረው በረከት፥ በዮሴፍ ራስ ላይ፥ ከወንድሞቹም በከበረው በእርሱ ራስ ላይ ይውረድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድር በምታስገኘው ምርጥ ስጦታና በሙላቷ፣ በሚቃጠለው ቍጥቋጦም ውስጥ በነበረው በርሱ ሞገስ። እነዚህ ሁሉ በወንድሞቹ መካከል ገዥ በሆነው፣ በዮሴፍ ዐናት ላይ ይውረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድሪቱም ገናንነትና ሞላዋ፥ በቁጥቋጦው ውስጥ ከነበረው በረከት በዮሴፍ ራስ ላይ፥ ከወንድሞቹም በተለየው ራስ አናት ላይ ይውረድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድራቸው ምርጥ በሆነ ነገር ሁሉ የተመላ ይሁን፤ በሚቃጠለው ቊጥቋጦ ውስጥ ከተገለጠው አምላክ ጸጋ ይብዛለት። ከወንድሞቹ መካከል ግንባር ቀደም ለሆነው ልዑል ለዮሴፍ ይደረግለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድሪቱም ገናንነትና ሞላዋ፥ 2 በቁጥቍጦው ውስጥ ከነበረው በረከት 2 በዮሴፍ ራስ ላይ፥ ከወንድሞቹም በተለየው ራስ አናት ላይ ይውረድ። |
እነዚያ ይስማኤላውያን ነጋዴዎችም ሲያልፉ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ ጐትተው አወጡት፤ ለይስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
ወንድሞቹም፥ “በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ገዢ ትሆነን ይሆን?” አሉት። እንደገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ የበለጠ ጠሉት።
ለእርሱም ለብቻው አቀረቡ፤ ለእነርሱም ለብቻቸው፤ ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ለግብፅ ሰዎችም ለብቻቸው፤ የግብፅ ሰዎች ከዕብራውያን ጋር መብላት አይችሉምና፥ ይህ ለግብፅ ሰዎች እንደ መርከስ ነውና።
የአባትህና የእናትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ይበልጣሉ፤ ዘለዓለማውያን ከሆኑ ከኮረብቶችም በረከቶች ይልቅ ኀያላን ናቸው፤ እነርሱም በዮሴፍ ራስ ላይ ይሆናሉ፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ራስ አናት ላይ ይሆናሉ።
የፈረሶቹን የሩጫ ድምፅ ከዳን ሰማን፤ ከሠራዊቱ ፈረሶች ሩጫ ድምፅ የተነሣም ምድር በመላዋ ተንቀጠቀጠች፤ መጥተውም ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማዪቱንና የተቀመጡባትንም በሉ።
የአሴር ልጆች በየወገናቸው፤ ከኢያምን የኢያምናውያን ወገን፥ ከኢያሱ የኢያሱያውያን ወገን፥ ከበርያ የበርያውያን ወገን።
ስለ ሙታን ግን እንዲነሡ እግዚአብሔር ‘እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤’ እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቍጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን?
“በእኛ ላይ አለቃና ፈራጅ ማን አድርጎሃል? ብለው የካዱትን ያን ሙሴን በቍጥቋጦው መካከል በታየው በመልአኩ እጅ እርሱን መልእክተኛና አዳኝ አድርጎ እግዚአብሔር ላከው።
እንግዲህ “ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው” ያላችሁ ቢኖር ግን፥ ስለ ነገራችሁና ባልንጀራችሁም የሚጠራጠር ስለሆነ አትብሉ።
ቅዱስና ያለ ተንኰል፥ ነውርም የሌለበት፥ ከኀጢአተኞችም የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል።