Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 37:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ሰዎች ግን ዮሴ​ፍን በግ​ብፅ ለፈ​ር​ዖን ጃን​ደ​ረባ ለዘ​በ​ኞቹ አለቃ ለጲ​ጥ​ፋራ ሸጡት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 በዚህ ጊዜ፣ የምድያም ነጋዴዎች ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወስደው፣ ከፈርዖን ሹማምት አንዱ ለነበረው ለዘበኞች አለቃ፣ ለጲጥፋራ ሸጡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እነዚያ የምድያም ሰዎች ግን ዮሴፍን በግብጽ ለፈርዖን ጃንደረባ ለዘበኞቹ አለቃ ለጶጥፋራ ሸጡት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 በዚያን ጊዜ የምድያም ሰዎች እስማኤላውያን ዮሴፍን በግብጽ አገር ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር ከፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ የሆነ የዘበኞቹ አለቃ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እነዚያ የምድያም ሰዎች ግን ዮሴፍን በግብፅ ለፈርዖን ጃንደረባ ለዘበኞቹ አለቃ ለዺጥፋራ ሸጡት።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 37:36
12 Referencias Cruzadas  

የእ​ስር ቤቱ ዘበ​ኞች አለ​ቃም ለዮ​ሴፍ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ያገ​ለ​ግ​ላ​ቸው ነበር፤ በግ​ዞት ቤትም አንድ ዓመት ተቀ​መጡ።


እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ዴ​ዎ​ችም ሲያ​ልፉ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ ጐት​ተው አወ​ጡት፤ ለይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ዮሴ​ፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነ​ር​ሱም ዮሴ​ፍን ወደ ግብፅ ወሰ​ዱት።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ጠጋ መጻ​ተኛ፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሕ​ዝቡ ይለ​የ​ኛል” አይ​በል፤ ጃን​ደ​ረ​ባም፥ “እነሆ፥ እኔ እንደ ደረቀ ዛፍ ነኝ” አይ​በል።


በባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዐ​ሥራ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ፊት የሚ​ቆ​መው የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።


በእ​ስር ቤት ውስ​ጥም ዮሴፍ ታስሮ በነ​በ​ረ​በት የግ​ዞት ስፍራ አጋ​ዛ​ቸው።


በዚ​ያም የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች አለቃ አገ​ል​ጋይ የሆነ አንድ ዕብ​ራዊ ጐል​ማሳ ከእኛ ጋር ነበር፤ ለእ​ር​ሱም ነገ​ር​ነው፤ ሕል​ማ​ች​ን​ንም ተረ​ጐ​መ​ልን።


ምድር ተከ​ፈ​ተች፥ ዳታ​ን​ንም ዋጠ​ችው፥ የአ​ቤ​ሮ​ን​ንም ወገን ደፈ​ነች፤


የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ፥ ኰብ​ል​ለ​ውም ወደ እርሱ የገ​ቡ​ትን ሰዎ​ችና የቀ​ረ​ው​ንም የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ወደ ባቢ​ሎን ማረ​ካ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios