Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 33:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በምድሪቱም ገናንነትና ሞላዋ፥ በቁጥቋጦው ውስጥ ከነበረው በረከት በዮሴፍ ራስ ላይ፥ ከወንድሞቹም በተለየው ራስ አናት ላይ ይውረድ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ምድር በምታስገኘው ምርጥ ስጦታና በሙላቷ፣ በሚቃጠለው ቍጥቋጦም ውስጥ በነበረው በርሱ ሞገስ። እነዚህ ሁሉ በወንድሞቹ መካከል ገዥ በሆነው፣ በዮሴፍ ዐናት ላይ ይውረዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ምድራቸው ምርጥ በሆነ ነገር ሁሉ የተመላ ይሁን፤ በሚቃጠለው ቊጥቋጦ ውስጥ ከተገለጠው አምላክ ጸጋ ይብዛለት። ከወንድሞቹ መካከል ግንባር ቀደም ለሆነው ልዑል ለዮሴፍ ይደረግለት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በየ​ወ​ቅ​ቱም ከም​ድ​ሪቱ ምላት፥ በቍ​ጥ​ቋ​ጦው ውስጥ ከነ​በ​ረው በረ​ከት፥ በዮ​ሴፍ ራስ ላይ፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም በከ​በ​ረው በእ​ርሱ ራስ ላይ ይው​ረድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በምድሪቱም ገናንነትና ሞላዋ፥ 2 በቁጥቍጦው ውስጥ ከነበረው በረከት 2 በዮሴፍ ራስ ላይ፥ ከወንድሞቹም በተለየው ራስ አናት ላይ ይውረድ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 33:16
22 Referencias Cruzadas  

የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።


እነዚያ የምድያም ሰዎች ግን ዮሴፍን በግብጽ ለፈርዖን ጃንደረባ ለዘበኞቹ አለቃ ለጶጥፋራ ሸጡት።


ወንድሞቹም፦ “በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ልትገዛ ይሆን?” አሉት። እንደገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ የበለጠ ጠሉት።


ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት፤ ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ግብፃውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ነበር።


የአባትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፥ ዘላለማውያን ከሆኑ ከኮረብቶችም በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፥ እነርሱም በዮሴፍ ራስ ላይ ይሆናሉ፥ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው ራስ አናት ላይ።


የዳዊት መዝሙር። ምድርና ሞላዋ የጌታ ናቸው፥ ዓለምና በእርሷም የሚኖሩ ሁሉ።


ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና።


አንተ ረዓብን እንደ ተገደለ አዋረድኸው፥ በኃያሉ ክንድህ ጠላቶችህን በተንሃቸው።


ሴቲቱም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅም ወለደች፤ መልካምም እንደሆነ ባየች ጊዜ ሦስት ወር ሸሸገችው።


“የፈረሶቻቸው ድምፅ ከዳን ተሰማ፤ ከአርበኞች ፈረሶች ማሽካካት የተነሣ ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች፤ መጡም ምድሪቱንና በእርሷም ያለውን ሁሉ፥ ከተማይቱንና የተቀመጡባትንም በሉ።


በየወገናቸው የዮሴፍ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ምናሴና ኤፍሬም።


ስለ ሙታን ግን እንደሚነሡ እግዚአብሔር “እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤” እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቁጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን?


“ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን! ሰላምም ደስ በሚሰኝባቸው ሰዎች መካከል በምድር ይሁን!” አሉ።


“‘ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው?’ ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቁጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።


ምድር የጌታ ነውና፥ በእርሷ የሞላባት ሁሉ።


ማንም ግን “ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው፤” ቢላችሁ ይህን በነገራችሁ ሰው ምክንያትና በኅሊናም ምክንያት ሥጋውን አትብሉ፤


እንዲህ ያለው ቅዱስ፥ ነቀፋ የሌለበት፥ ንጹሕ፥ ከኃጢአተኞች የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ ሊቀ ካህናት ሊኖረን ይገባል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos