የሶርህያም ልጅ አቢሳ አዳነው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ወግቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፥ “አንተ የእስራኤል መብራት እንዳትጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም” ብለው ማሉለት።
ዘዳግም 31:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አላቸውም፥ “እኔ ዛሬ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከዚህ በኋላ እወጣና እገባ ዘንድ አልችልም፤ እግዚአብሔርም፦ ‘ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርም’ ብሎኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከእንግዲህ ልወጣና ልገባ አልችልም፤ እግዚአብሔርም ‘ዮርዳኖስን አትሻገርም’ ብሎኛል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፤ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከእንግዲህ ልወጣና ልገባ አልችልም፤ ጌታም ‘ዮርዳኖስን አትሻገርም’ ብሎኛል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ የእኔ ዕድሜ መቶ ኻያ ዓመት ስለ ሆነ ከእንግዲህ ወዲህ እናንተን መምራት አይቻለኝም፤ ከዚህም በላይ እኔ ዮርዳኖስን እንደማልሻገር እግዚአብሔር ነግሮኛል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አላቸውም፦ እኔ ዛሬ መቶ ሀያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከዚህ በኋላ እወጣና እገባ ዘንድ አልችልም፤ እግዚአብሔርም፦ ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርም ብሎኛል። |
የሶርህያም ልጅ አቢሳ አዳነው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ወግቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፥ “አንተ የእስራኤል መብራት እንዳትጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም” ብለው ማሉለት።
አሁንም አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እኔን ባሪያህን በአባቴ በዳዊት ፋንታ አንግሠኸኛል፤ እኔም መውጫዬንና መግቢያዬን የማላውቅ ታናሽ ብላቴና ነኝ።
እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፥ “በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋችሁ ምድር ይህን ማኅበር ይዛችሁ አትገቡም” አላቸው።
በፊታቸው የሚወጣውንና የሚገባውን፥ የሚያስወጣቸውንና፥ የሚያስገባቸውንም፥ የእግዚአብሔር ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን።”
አሁንም እነሆ፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሰበክሁላችሁ እናንተ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንደማታዩኝ እኔ ዐውቄአለሁ።