Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 20:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት የሰ​በ​ክ​ሁ​ላ​ችሁ እና​ንተ ሁላ​ችሁ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን እን​ደ​ማ​ታ​ዩኝ እኔ ዐው​ቄ​አ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “አሁንም ቢሆን፣ በመካከላችሁ ተዘዋውሬ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሰበክሁላችሁ፣ እናንተ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲያ ፊቴን እንደማታዩ ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 አሁንም እነሆ፥ እኔ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንዳትዩ አውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “እስከ አሁን በእናንተ ሁሉ መካከል እየተዘዋወርኩ የእግዚአብሔርን መንግሥት እሰብክ ነበር፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን ከእናንተ ማንም ከቶ ፊቴን እንደማያይ ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አሁንም፥ እነሆ፥ እኔ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንዳትዩ አውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 20:25
13 Referencias Cruzadas  

ማንም ሳይ​ከ​ለ​ክ​ለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ይሰ​ብክ ነበር፤ ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም እጅግ ገልጦ ያስ​ተ​ምር ነበር።


ይል​ቁ​ንም “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን አታ​ዩ​ትም” ስለ አላ​ቸው እጅግ አዘኑ። እስከ መር​ከ​ብም ድረስ ሸኙት።


ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።


ስለ እና​ንተ እና በሎ​ዶ​ቅያ ስላሉ፥ ፊቴ​ንም በሥጋ ስላ​ላ​ዩት ምእ​መ​ናን ሁሉ ምን ያህል እን​ደ​ም​ጋ​ደል ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ።


በክ​ር​ስ​ቶ​ስም ያሉት የይ​ሁዳ ሀገር ማኅ​በረ ክር​ስ​ቲ​ያን ፊቴን አያ​ው​ቁም ነበር።


አሁን ግን በዚህ ሀገር ሥራ​ዬን ስለ ጨረ​ስሁ፥ ከብዙ ጊዜም ጀምሮ ወደ እና​ንተ ልመጣ እተጋ ስለ ነበር፤


ነገር ግን ፊል​ጶስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትና ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሰብ​ኮ​ላ​ቸው በአ​መኑ ጊዜ ሴቶ​ችም ወን​ዶ​ችም ተጠ​መቁ።


“ኦሪ​ትም ነቢ​ያ​ትም ከጥ​ንት ጀምሮ እስከ ዮሐ​ንስ ድረስ ነበሩ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ይሰ​በ​ካል፤ ሁሉም ወደ እር​ስዋ ይጋ​ፋል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሙታ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ብሩ ዘንድ ሙታ​ንን ተዉ​አ​ቸው፤ አንተ ግን ሂድና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ስበክ” አለው።


እርሱም “ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ ሁሉ ከመዝገቡ አዲሱንና አሮጌውን የሚያወጣ ባለቤትን ይመስላል፤” አላቸው።


የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፤ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።


ሄዳችሁም ‘መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች፤’ ብላችሁ ስበኩ።


ከዚያ ዘመን ጀምሮኢየሱስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” እያለ ይሰብክ ጀመር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios