Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 21:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ አቢሳ አዳ​ነው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ወግቶ ገደ​ለው። ያን​ጊ​ዜም የዳ​ዊት ሰዎች፥ “አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል መብ​ራት እን​ዳ​ት​ጠፋ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰ​ልፍ አት​ወ​ጣም” ብለው ማሉ​ለት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን ዳዊትን ለመታደግ መጣ፤ ፍልስጥኤማዊውንም ወግቶ ገደለው። ከዚያም የዳዊት ሰዎች፣ “የእስራኤል መብራት እንዳይጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋራ ወደ ጦርነት መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን ዳዊትን ለመታደግ መጣ፤ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። ከዚያም የዳዊት ሰዎች፥ “የእስራኤል መብራት እንዳይጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ነገር ግን የጸሩያ ልጅ አቢሳ ዳዊትን ለመርዳት መጥቶ በዚያ ኀያል ሰው ላይ አደጋ በመጣል ገደለው፤ ከዚያን በኋላ የዳዊት ተከታዮች ዳግመኛ ከእነርሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዳይሄድ ዳዊትን ቃል በማስገባት “የእስራኤል መብራት የሆንክ አንተ እንዳትጠፋ ዳግመኛ ወደ ጦርነት አትወጣም” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የጽሩያም ልጅ አቢሳ አዳነው፥ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፦ አንተ የእስራኤልን መብራት እንዳታጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም ብለው ማሉለት።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 21:17
14 Referencias Cruzadas  

ስሜ​ንም ባኖ​ር​ሁ​ባት በዚ​ያች በመ​ረ​ጥ​ኋት ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለባ​ሪ​ያዬ ለዳ​ዊት በፊቴ ሁል​ጊዜ መብ​ራት ይሆ​ን​ለት ዘንድ ለልጁ ሁለት ነገ​ድን እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።


እነ​ርሱ ግን “አንተ ከእኛ ከሁ​ላ​ችን ይልቅ እንደ ዐሥር ሽህ ሠራ​ዊት ስለ​ሆ​ንህ ብን​ሸሽ ልባ​ቸው አይ​ከ​ተ​ለ​ን​ምና፥ እኩ​ሌ​ታ​ች​ንም ብን​ሞት ልባ​ቸው አይ​ከ​ተ​ለ​ን​ምና አት​ውጣ፤ አሁ​ንም መር​ዳ​ትን ትረ​ዳን ዘንድ በከ​ተማ ብት​ኖ​ር​ልን ይሻ​ለ​ናል” አሉት።


ነገር ግን ልጁን ከእ​ርሱ በኋላ ያስ​ነሣ ዘንድ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ያጸና ዘንድ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ዳዊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መብ​ራ​ትን አደ​ረ​ገ​ለት፤


እርሱ የሚ​ነ​ድና የሚ​ያ​በራ መብ​ራት ነበረ፤ እና​ን​ተም አን​ዲት ሰዓት በብ​ር​ሃኑ ደስ ሊላ​ችሁ ወደ​ዳ​ችሁ።


አቤቱ፥ ፍጥ​ረ​ትህ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፥ ጻድ​ቃ​ን​ህም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።


አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ፥ እጆ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ብ​ጭቡ፥ በደ​ስታ ቃልም ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ።


አቤቱ! አንተ መብ​ራቴ ነህና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጨለ​ማ​ዬን ያበ​ራ​ል​ኛ​ልና።


በመ​ከ​ራዬ ቀን ደረ​ሱ​ብኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ደጋ​ፊዬ ሆነ።


እነ​ሆም፥ ዘመ​ዶች ሁሉ በባ​ሪ​ያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደ​ለው ስለ ወን​ድሙ ነፍስ እን​ገ​ድ​ለው ዘንድ ወን​ድ​ሙን የገ​ደ​ለ​ውን አውጪ አሉኝ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ይ​ቀር ወራ​ሹን የቀ​ረ​ውን መብ​ራ​ቴን ያጠ​ፋሉ፤”


የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ “እባ​ክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያ​ውቅ የና​ታ​ን​ያን ልጅ እስ​ማ​ኤ​ልን ልግ​ደ​ለው፤ ወደ አንተ የተ​ሰ​በ​ሰቡ አይ​ሁድ ሁሉ እን​ዲ​በ​ተኑ፥ የይ​ሁ​ዳም ቅሬታ እን​ዲ​ጠፋ ነፍ​ስ​ህን ስለ ምን ይገ​ድ​ላል?” ብሎ በመ​ሴፋ በቈ​ይታ ለጎ​ዶ​ል​ያስ ተና​ገረ።


ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን ከኢ​ዮ​አብ እጅ በታች ሢሶ​ውን፥ ከኢ​ዮ​አ​ብም ወን​ድም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከአ​ቢሳ እጅ በታች ሢሶ​ውን፥ ከጌት ሰውም ከኤቲ እጅ በታች ሢሶ​ውን ላከ። ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን፥ “እኔ ደግሞ ከእ​ና​ንተ ጋር እወ​ጣ​ለሁ” አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios