እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ይቈርጥሃል፤ በዕንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤ የሰማይ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”
ዘዳግም 21:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ማንም ሰው ለሞት የሚያበቃውን ኀጢአት ቢሠራ፥ እንዲሞትም ቢፈረድበት፥ በእንጨትም ላይ ብትሰቅለው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ በደል ፈጽሞ ቢገደልና በድኑ በዕንጨት ላይ ቢሰቀል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንደ ሰው ለሞት የሚያበቃ በደል ፈጽሞ ቢገደልና በድኑ በዕንጨት ላይ ቢሰቀል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው በሠራው ከባድ ወንጀል ምክንያት በእንጨት በስቅላት ቢቀጣ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም ሰው ለሞት የሚያበቃውን ኃጢአት ቢሠራ፥ እንዲሞትም ቢፈረድበት፥ በእንጨትም ላይ ብትሰቅለው፥ |
እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ይቈርጥሃል፤ በዕንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤ የሰማይ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”
የኢዮሔል ልጅ ሩጻፋም ማቅ ወስዳ ከመከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰማይ እስኪዘንብ ድረስ በድንጋይ ላይ ዘረጋችው፤ በቀንም የሰማይ ወፎች፥ በሌሊትም የዱር አራዊት ያርፉባቸው ዘንድ አልተወችም።
ከልጆቹ ሰባት ሰዎች ስጠንና ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል ሀገር በገባዖን ለእግዚአብሔር እንሠቅላቸዋለን።” ንጉሡም፥ “እሰጣችኋለሁ” አለ።
በገባዖንም ሰዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ በእግዚአብሔርም ፊት በተራራው ላይ ሰቀሏቸው። ሰባቱም በአንድነት ወደቁ፤ እህል በሚታጨድበትም ወራት በገብሱ መከር መጀመሪያ ተገደሉ።
ዳዊትም ጐልማሶቹን አዘዘ፤ ገደሉአቸውም፤ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ቈርጠው በኬብሮን በውኃ መቆሚያ አጠገብ አንጠለጠሉአቸው። የኢያቡስቴን ራስ ግን ወስደው በአበኔር መቃብር በኬብሮን ቀበሩት።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስላፈረሱ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ በፀሐይ ፊት ቅጣቸው። የእግዚአብሔርም ቍጣ ከእስራኤል ይርቃል።”
ቀራንዮ ወደሚባለው ቦታ በደረሱ ጊዜም፥ በዚያ ሰቀሉት፤ እነዚያንም ሁለት ወንበዴዎች አንዱን በቀኙ አንዱንም በግራው ሰቀሉ።
ከበደልሁ ወይም ለሞት የሚያበቃኝ የሠራሁት ክፉ ሥራ ካለ ሞት አይፈረድብኝ አልልም፤ ነገር ግን እነዚህ በደል የሌለብኝን በከንቱ የሚከስሱኝ ከሆነ፥ ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ ለማን ይቻለዋል? እኔ ወደ ቄሣር ይግባኝ ብያለሁ።”
እኔ ግን ለሞት የሚያደርሰው በደል እንዳልሠራ እጅግ መርምሬ፥ እርሱም ራሱ ወደ ቄሣር ይግባኝ ማለትን ስለወደደ እንግዲህ ልልከው ቈርጫለሁ።
ለብቻቸውም ገለል ብለው እርስ በርሳቸው እንዲህ ብለው ተነጋገሩ፥ “ይህ ሰው እንዲሞት ወይም እንዲታሰር የሚያበቃ የሠራው በደል የለም።”
ባለ ደሙ ነፍሰ ገዳዩን በልቡ ተናድዶ እንዳያሳድደው መንገዱም ሩቅ ስለሆነ አግኝቶ እንዳይገድለው፥ አስቀድሞ ጠላቱ አልነበረምና ሞት አይገባውም።
በብላቴናዪቱ ላይ ግን ምንም አታድርጉ፤ በብላቴናዪቱ ላይ ለሞት የሚያበቃ ኀጢአት የለባትም፤ ሰው በባልንጀራው ላይ ተነሥቶ እንደሚገድለው ይህ ነገር ደግሞ እንደዚሁ ነውና፤
ከዚህም በኋላ መትተው ገደሉአቸው፤ በአምስቱም ዛፎች ላይ ሰቀሉአቸው፤ እስከ ማታም ደረስ በዛፎቹ ላይ ተሰቅለው ቈዩ።
ፀሐይም ልትገባ በቀረበች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፤ ከዛፎችም አወረዱአቸው፤ ተሸሽገውም በነበሩበት ዋሻ ጣሉአቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዋሻው አፍ ታላላቅ ድንጋይ ተደርጎአል።
የጋይንም ንጉሥ በዝግባ ዛፍ ላይ ሰቀለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ ያወርዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛፉም አወረዱት፤ በከተማዪቱም በር አደባባይ ጣሉት፤ በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት።
ይህ ያደረግኸው ነገር መልካም አይደለም፤ ሕያው እግዚአብሔርን! እናንተ እግዚአብሔር የቀባውን ጌታችሁን አልጠበቃችሁምና ሞት ይገባችኋል፤ አሁንም የንጉሡ ጦርና በራሱ አጠገብ የነበረው የውኃ መንቀል የት እንደ ሆነ ተመልከት” አለው።