Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ኢያሱ 8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የጋይ ከተማ መደ​ም​ሰስ

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግጥ፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችን ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤ ተነ​ሥ​ተ​ህም ወደ ጋይ ውጣ፤ እነሆ፥ የጋ​ይ​ንም ንጉሥ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ከተ​ማ​ው​ንም ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።

2 በኢ​ያ​ሪ​ኮና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እን​ዲሁ በጋ​ይና በን​ጉ​ሥዋ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የከ​ብ​ቱን ምርኮ ግን ለራ​ሳ​ችሁ ትዘ​ር​ፋ​ላ​ችሁ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በስ​ተ​ኋላ ይከ​ብ​ቧት ዘንድ ጦር ላክ” አለው።

3 ኢያ​ሱም፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ቹም ሕዝብ ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ወደ ጋይ ወጡ፤ ኢያ​ሱም ጽኑ​ዓን፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ችና ኀያ​ላን የሆ​ኑ​ትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ፤ በሌ​ሊ​ትም ላካ​ቸው።

4 እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እነሆ፥ ሂዱና ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ኋላ ተደ​በቁ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ አት​ራቁ፤ ሁላ​ች​ሁም ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ችሁ ተቀ​መጡ፤

5 እኔ፥ ከእ​ኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤ የጋ​ይም ሰዎች እኛን ሊገ​ናኙ እንደ ፊተ​ኛው በወጡ ጊዜ ከፊ​ታ​ቸው እን​ሸ​ሻ​ለን፤

6 ወጥ​ተ​ውም በተ​ከ​ተ​ሉን ጊዜ ከከ​ተማ እና​ር​ቃ​ቸ​ዋ​ለን፤ እነ​ር​ሱም እንደ በፊቱ ከፊ​ታ​ችን ሸሹ ይላሉ፤ እኛም ከፊ​ታ​ቸው እን​ሸ​ሻ​ለን።

7 እን​ግ​ዲህ እና​ን​ተም ከተ​ደ​በ​ቃ​ች​ሁ​በት ስፍራ ተነሡ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ስ​ዋን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ልና ከተ​ማ​ዪ​ቱን ያዙ።

8 በያ​ዛ​ች​ኋ​ትም ጊዜ ከተ​ማ​ዪ​ቱን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉ​አት፤ እንደ አል​ኋ​ችሁ አድ​ርጉ፤ እነሆ፥ አዝ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።”

9 ኢያ​ሱም ላካ​ቸው፤ ወደ​ሚ​ደ​በ​ቁ​በ​ትም ስፍራ ሄዱ፤ በጋ​ይና በቤ​ቴል መካ​ከ​ልም በጋይ በባ​ሕር በኩል ተቀ​መጡ፤ ኢያሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሕ​ዝቡ መካ​ከል አደረ።

10 ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አያ​ቸው፤ እር​ሱም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከሕ​ዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።

11 ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ተዋ​ጊ​ዎች ሕዝብ ሁሉ ወጥ​ተው ቀረቡ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ፊት ደረሱ፤ በጋ​ይም በም​ሥ​ራቅ በኩል ሰፈሩ፤ በእ​ነ​ር​ሱና በጋ​ይም መካ​ከል ሸለቆ ነበረ።

12 ኢያ​ሱም አም​ስት ሺህ ሰዎ​ችን ወስዶ በቤ​ቴ​ልና በጋይ መካ​ከል በጋይ ባሕር በኩል ይከ​ብቡ ዘንድ አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው።

13 ሕዝ​ቡም ሁሉ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን በከ​ተ​ማው መስዕ በኩል አኖሩ፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ከተ​ማው ባሕር ድረስ ነው፤ ኢያ​ሱም በዚ​ያች ሌሊት ወደ ሸለ​ቆው መካ​ከል ሄደ።

14 የጋ​ይም ንጉሥ በሰማ ጊዜ ፈጥኖ ሄደ። የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ወጡ፤ እር​ሱና ሕዝ​ቡም ሁሉ በተ​ወ​ሰ​ነው ጊዜ በዓ​ረባ ፊት ባለው አንድ ስፍራ እስ​ራ​ኤ​ልን በጦ​ር​ነት ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ እርሱ ግን ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ኋላ እንደ ተደ​በቁ አያ​ው​ቅም ነበር።

15 በደ​ረ​ሱ​ባ​ቸ​ውም ጊዜ ኢያ​ሱና እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከፊ​ታ​ቸው አፈ​ገ​ፈጉ፤ በም​ድረ በዳው መን​ገ​ድም ሸሹ።

16 የሀ​ገ​ሪ​ቱም ሰዎች ሁሉ ተጠሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ተከ​ት​ለው አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እን​ዲ​ርቁ አደ​ረ​ጓ​ቸው።

17 በጋ​ይና በቤ​ቴ​ልም ውስጥ እስ​ራ​ኤ​ልን ለማ​ሳ​ደድ ያል​ወጣ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ከፍ​ተው ተዉ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አሳ​ደ​ዱት።

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ጋይን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለ​ሁና በእ​ጅህ ያለ​ውን ጦር በላ​ይዋ ዘርጋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም የከ​በ​ቡ​አት ፈጥ​ነው ከስ​ፍ​ራ​ቸው ይነ​ሣሉ” አለው፤ ኢያ​ሱም በከ​ተ​ማዋ ላይ በእጁ ያለ​ውን ጦር ዘረጋ።

19 የተ​ደ​በ​ቁ​ትም ፈጥ​ነው ከስ​ፍ​ራ​ቸው ተነሡ፤ ኢያ​ሱም እጁን በዘ​ረጋ ጊዜ ወጡ፤ ወደ ከተ​ማ​ዋም ገብ​ተው ያዙ​አት፤ ፈጥ​ነ​ውም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉ​አት።

20 የጋ​ይም ሰዎች ወደ ኋላ​ቸው ዞረው በተ​መ​ለ​ከቱ ጊዜ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወዲ​ህና ወዲያ መሸሽ አል​ቻ​ሉም፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው ላይ ተመ​ለሱ።

21 ኢያሱ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተደ​ብ​ቀው የነ​በ​ሩት ከተ​ማ​ዪ​ቱን እንደ ያዙ፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ ባዩ ጊዜ ወደ​ኋላ ተመ​ል​ሰው የጋ​ይን ሰዎች ገደ​ሉ​አ​ቸው።

22 እነ​ዚ​ያም ከከ​ተማ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሠራ​ዊት መካ​ከ​ልም አገ​ቡ​አ​ቸው፤ እኒያ ከወ​ዲያ፥ እኒ​ህም ከወ​ዲህ ሆነው አንድ እን​ኳን ሳይ​ቀ​ርና ሳያ​መ​ልጥ ገደ​ሉ​አ​ቸው።

23 የጋ​ይ​ንም ንጉሥ ሳይ​ሞት ይዘው ወደ ኢያሱ አመ​ጡት።

24 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተከ​ት​ለ​ዋ​ቸው በነ​በ​ረ​በት በተ​ራ​ራው ቍል​ቍ​ለ​ትና በም​ድረ በዳ የጋ​ይን ሰዎች መግ​ደ​ልን ከጨ​ረሱ፥ ሁሉ​ንም በጦር ወግ​ተው ከአ​ጠ​ፉ​አ​ቸው በኋላ ኢያሱ ወዲ​ያ​ውኑ ወደ ጋይ ተመ​ልሶ፥ በሰ​ይፍ አጠ​ፋት።

25 በዚ​ያም ቀን የወ​ደ​ቁት ሁሉ ወን​ድም፥ ሴትም፥ የጋይ ሰዎች ሁሉ ዐሥራ ሁለት ሺህ ነፍስ ነበሩ።

26 ኢያ​ሱም የጋ​ይን ሰዎች እስ​ኪ​ያ​ጠፋ ድረስ ጦር የዘ​ረ​ጋ​በ​ትን እጁን አላ​ጠ​ፈም።

27 ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እን​ዳ​ዘ​ዘው የዚ​ያ​ችን ከተማ ከብ​ትና ምርኮ ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለራ​ሳ​ቸው ዘረፉ፤

28 ኢያ​ሱም ከተ​ማ​ዋን በእ​ሳት አቃ​ጠ​ላት፤ ዐመ​ድም ሆነች፤ እስከ ዛሬም ድረስ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ የሚ​ኖ​ር​ባት እን​ዳ​ይ​ኖር አደ​ረ​ጋት።

29 የጋ​ይ​ንም ንጉሥ በዝ​ግባ ዛፍ ላይ ሰቀ​ለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐ​ይም በገ​ባች ጊዜ ኢያሱ ያወ​ር​ዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛ​ፉም አወ​ረ​ዱት፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር አደ​ባ​ባይ ጣሉት፤ በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ​ውን ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ሩ​በት።


የሙሴ ሕግ በጌ​ባል ተራራ መነ​በቡ

30 የዚያ ጊዜም ኢያሱ በጌ​ባል ተራራ ላይ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያን ሠራ።

31 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዳ​ዘዘ፥ በሙ​ሴም ሕግ መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው፥ መሠ​ዊ​ያው ካል​ተ​ወ​ቀ​ረና ብረት ካል​ነ​ካው ድን​ጋይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ።

32 ኢያ​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት በድ​ን​ጋ​ዮቹ ላይ ሙሴ የጻ​ፈ​ውን ይህን ሁለ​ተ​ኛ​ውን ሕግ በድ​ን​ጋ​ዮች ላይ ጻፈ።

33 የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሕዝብ አስ​ቀ​ድሞ ይባ​ር​ኩ​አ​ቸው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ እን​ዳ​ዘዘ፥ እስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የሀ​ገሩ ልጆ​ችም፥ መጻ​ተ​ኞ​ችም እኩ​ሌ​ቶቹ በገ​ሪ​ዛን ተራራ አጠ​ገብ፥ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም በጌ​ባል ተራራ አጠ​ገብ ሆነው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦተ ሕግ በተ​ሸ​ከ​ሙት በሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ፊት ለፊት፥ በታ​ቦ​ቱም ፊት በግ​ራና በቀኝ ቆመው ነበር።

34 ከዚ​ህም በኋላ ኢያሱ በሙሴ ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ፥ የሕ​ጉን ቃሎች ሁሉ በረ​ከ​ቱ​ንና ርግ​ማ​ኑን አነ​በበ።

35 ኢያ​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ፥ በወ​ን​ዶ​ቹም፥ በሴ​ቶ​ቹም፥ በሕ​ፃ​ና​ቱም፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም በሚ​ኖ​ሩት መጻ​ተ​ኞች ፊት ሙሴ ካዘ​ዘው ያላ​ነ​በ​በ​ውና ያላ​ሰ​ማው ቃል የለም።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos