ጌታው ወደ ቤተ እግዚአብሔር ፈራጆች ይውሰደው፤ ወደ ደጁም፥ ወደ መቃኑም አቅርቦ አፍንጫውን በወስፌ ይብሳው፤ ለዘለዓለምም ባሪያው ይሁነው።
ዘዳግም 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱ ጠበኞች በእግዚአብሔር ፊት በካህናቱና በዚያ ዘመን በሚፈርዱ ፈራጆች ፊት ይቆማሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክርክሩ የሚመለከታቸው ሁለቱ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት፣ በዚያ ወቅት በሚያገለግሉት ካህናትና ፈራጆች ፊት ይቁሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱም ወገኖች በጌታ ፊት፥ በዚያ ወቅት በሚያገለግሉት ካህናትና ፈራጆች ፊት ይቁሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱም ወገኖች እግዚአብሔር በሚመለክበት ቦታ ወደሚገኙት የወቅቱ ካህናትና ዳኞች ወደሆኑት ፊት ይቅረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱ ጠበኞች በእግዚአብሔር ፊት በካህናቱና በዚያ ዘመን በሚፈርዱ ፈራጆች ፊት ይቆማሉ፤ |
ጌታው ወደ ቤተ እግዚአብሔር ፈራጆች ይውሰደው፤ ወደ ደጁም፥ ወደ መቃኑም አቅርቦ አፍንጫውን በወስፌ ይብሳው፤ ለዘለዓለምም ባሪያው ይሁነው።
ሌባው ባይገኝ ባለቤቱ ወደ ፈጣሪ ፊት ይቅረብ፤ ባልንጀራው አደራ በአስቀመጠበት ገንዘብም ላይ እንዳልተተነኰለና ክፉ እንዳላሰበ ይማል።
ክርክርም በሆነ ጊዜ ለመፍረድ ይቁሙ፤ እንደ ፍርዴ ይፍረዱ፤ በበዓላቴ ሁሉ ሕጌንና ሥርዐቴን ይጠብቁ፤ ሰንበታቴንም ይቀድሱ።
ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።
“አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በሀገርህ ደጅ ሁሉ በየነገዶችህ ፈራጆችንና መባውን የሚጽፉትን ሹሙ፤ ለሕዝቡም ቅን ፍርድን ይፍረዱ።
የሌዊ ልጆች ካህናትም ይቀርባሉ፤ በፊቱ እንዲያገለግሉ፥ በስሙም እንዲባርኩ አምላክህ እግዚአብሔር መርጦአቸዋልና፤ በእነርሱም ቃል ክርክር ሁሉ ጕዳትም ሁሉ ይቆማልና፤