Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 22:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሌባው ባይ​ገኝ ባለ​ቤቱ ወደ ፈጣሪ ፊት ይቅ​ረብ፤ ባል​ን​ጀ​ራው አደራ በአ​ስ​ቀ​መ​ጠ​በት ገን​ዘ​ብም ላይ እን​ዳ​ል​ተ​ተ​ነ​ኰ​ለና ክፉ እን​ዳ​ላ​ሰበ ይማል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሌባው ካልተያዘ ግን፣ የቤቱ ባለቤት በንብረቱ ስርቆት ላይ እጁ ይኑርበት ወይም አይኑርበት ይታወቅ ዘንድ ዳኞች ፊት ይቅረብ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለ ሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ይህ የእኔ ነው ቢል ክርክራቸው ወደ እግዚአብሔር ይምጣ፤ እግዚአብሔርም የፈረደበት እርሱ ለባልንጀራው እጥፍ አድርጎ ይክፈል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሌባው ካልተገኘ ግን ዕቃውን በዐደራ የተቀበለው ሰው የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሆኑ ዳኞች ፊት ቀርቦ የዚያን ሰው ንብረት አለመስረቁን በመሐላ ያረጋግጥ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሌባውም ባይገኝ ባለቤቱ ወደ ፈራጆች ይቅረብ፥ እጁንም በባልንጀራው ከብት ላይ እንዳልዘረጋ ይማል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 22:8
9 Referencias Cruzadas  

“ሰው ባል​ጀ​ራ​ውን ቢበ​ድል፥ ይም​ልም ዘንድ በላዩ መሐላ ቢጫ​ን​በት፥ እር​ሱም መጥቶ በዚህ ቤት በመ​ሠ​ዊ​ያህ ፊት ቢና​ዘዝ፥


ከእ​ነ​ዚ​ህም ውስጥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ የሚ​ያ​ሠ​ሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድ​ስቱ ሺህም ጻፎ​ችና ፈራ​ጆች ነበሩ።


አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አት​በል፥ ቸልም አት​በል።


ጌታው ወደ ቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራ​ጆች ይው​ሰ​ደው፤ ወደ ደጁም፥ ወደ መቃ​ኑም አቅ​ርቦ አፍ​ን​ጫ​ውን በወ​ስፌ ይብ​ሳው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባሪ​ያው ይሁ​ነው።


“ፈራ​ጆ​ችን አት​ስ​ደብ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም አለቃ ክፉ አት​ና​ገ​ረው።


ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለ​ሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካ​ሰሱ፥ አን​ዱም፦ ‘ይህ የእኔ ነው’ ቢል፥ ክር​ክ​ራ​ቸው በፈ​ጣሪ ፊት ይቅ​ረብ፤ በፈ​ጣሪ ፊት የተ​ፈ​ረ​ደ​በት እርሱ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው እጥፍ ይክ​ፈል።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥህ በሀ​ገ​ርህ ደጅ ሁሉ በየ​ነ​ገ​ዶ​ችህ ፈራ​ጆ​ች​ንና መባ​ውን የሚ​ጽ​ፉ​ትን ሹሙ፤ ለሕ​ዝ​ቡም ቅን ፍር​ድን ይፍ​ረዱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos