ይህ ሕዝብ በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ቤት መሥዋዕትን ያቀርብ ዘንድ ቢወጣ፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ወደ ጌታቸው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ይመለሳል፥ እኔንም ይወጉኛል።”
ዘዳግም 12:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ከአንዱ ዘንድ በመረጠው ስፍራ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን አቅርብ፤ በዚያም ዛሬ እኔ የማዝዝህን ሁሉ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከነገዶችህ መካከል በአንዱ፣ እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ብቻ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችህን አቅርብ፤ እዚያም እኔ የማዝዝህን ሁሉ ጠብቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከነገዶችህ መካከል በአንዱ፥ ጌታ በሚመርጠው ስፍራ ብቻ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችህን አቅርብ፤ እዚያም እኔ የማዝህን ሁሉ ጠብቅ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሥዋዕትህን ሁሉ ማቅረብ የሚገባህ ከነገዶችህ መካከል የአንዱ ግዛት በሆነው ክፍል እና እግዚአብሔር በሚመርጠው በአንድ ስፍራ ብቻ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህንም ሆነ ሌላውንም እኔ ያዘዝኩህን ሁሉ በዚያ ስፍራ ብቻ ትፈጽማለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እግዚአብሔር ከነገዶችህ ከአንዱ ዘንድ በመረጠው ስፍራ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን አቅርብ፥ በዚያም የማዝዝህን ሁሉ አድርግ። |
ይህ ሕዝብ በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ቤት መሥዋዕትን ያቀርብ ዘንድ ቢወጣ፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ወደ ጌታቸው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ይመለሳል፥ እኔንም ይወጉኛል።”
ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆናል ወዳልኸው ስፍራ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ሌሊትና ቀን የተገለጡ ይሁኑ።
እናንተም፦ በአምላካችን በእግዚአብሔር እንታመናለን ብትሉኝ፥ ሕዝቅያስ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን፦ በኢየሩሳሌም ባለው በዚህ መሠዊያ ፊት ስገዱ ብሎ የኮረብታ መስገጃዎቹንና መሠዊያዎቹን ያስፈረሰ ይህ አይደለምን?
ዳዊትም፥ “ይህ የአምላኬ የእግዚአብሔር ቤት ነው፤ ይህም ለእስራኤል ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነው መሠዊያ ነው” አለ።
ከእስራኤል ቤት ከመካከላቸውም ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው በሬ፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ቢያርድ፥ በሰፈሩ ውስጥ ወይም ከሰፈሩ ውጭ ቢያርደው፥
ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው የተመረጠ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ ወይም የድኅነት መሥዋዕት ያደርገው ዘንድ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ በሌላም ቦታ ቢያርደው፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ለእግዚአብሔር ቍርባን ያቀርብ ዘንድ ወደ ምስክሩ ድንኳን ባያመጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈጠርበታል፤ ደም አፍስሶአልና፤ ያም ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።
ኀጢአታቸውን ይቅር ብሎ በደላቸውንም ሳያስብ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለሙን ከራሱ ጋር አስታርቆአልና፤ የዕርቅ ቃሉንም በእኛ ላይ አደረገ፤ የይቅርታውንም መልእክት ሰጠን።
በዚያን ጊዜ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ቍርባናችሁንም፥ ዐሥራታችሁንም፥ ከእጃችሁ ሥራ ቀዳምያቱን የተመረጠውንም መባችሁን ሁሉ፥ ለአምላካችሁም የተሳላችሁትን ሁሉ ውሰዱ።
“ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ሰጠህ በረከት፥ እንደ ፈቀድህ፥ በሀገርህ ሁሉ ውስጥ አርደህ ሥጋን ብላ፤ ከአንተ ንጹሕ ሰው፥ ንጹሕም ያልሆነ ሰው እንደ ሚዳቋና እንደ ዋላ ያለውን ይብላው።
ነገር ግን አንተ፥ ወንድና ሴት ልጅህም፥ ወንድና ሴት አገልጋይህም፥ በሀገርህም ውስጥ ያለው መጻተኛ አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ብሉት፤ እጅህንም በምትዘረጋበት ነገር ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበልህ።
ነገር ግን አምላካችሁ እግዚአብሔር ከከተሞቻችሁ ሁሉ በአንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመረጠውን ስፍራ ትሻላችሁ፤ ወደዚያም ትመጣላችሁ።
በዘመንህም ሁሉ አምላክህን እግዚአብሔርን መፍራትን ትማር ዘንድ፥ ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የእህልህን፥ የወይንህን፥ የዘይትህንም ዐሥራት፥ የላምህንና የበግህንም በኵራት ብላ።
አምላክህ እግዚአብሔር በዚያ ስሙ ይጠራበት ዘንድ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ፋሲካ ከበግና ከላም መንጋ ሠዋ።
“በደምና በደም መካከል፥ በፍርድና በፍርድ መካከል፥ በመቍሰልና በመቍሰል መካከል፥ በክርክርና በክርክር መካከል በሀገርህ ውስጥ ሰዎች ስለሚከራከሩበት ክርክር የሚሳንህ የፍርድ ነገር ቢኖር፥ አንተ ተነሥተህ ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ትወጣለህ፤
“አንድ ሌዋዊ ሰው ከሚቀመጥባቸው በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ካሉት ከተሞች ከአንዲቱ፥ በፍጹም ልብም ሊያገለግል እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ቢመጣ፥
እስራኤል ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ ዘንድ እርሱ በመረጠው ቦታ በአንድነት በሚሄድበት ጊዜ፥ ይህን ሕግ በእስራኤል ሁሉ ፊት በጆሮው አንብበው።
በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር ልናቀርብ አይገባንምን?
በድንኳኑ ፊት ካለው ከአምላካችን ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለሰላም መሥዋዕት፥ ለደኅንነት መሥዋዕትም የሚሆን መሠዊያን የሠራነው በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ እግዚአብሔርንም ዛሬ መከተልን ለመተው በማለት እንደ ሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።”
በዚያም ቀን ኢያሱ እነርሱን ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንጨት ቈራጮችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው። ስለዚህም የገባዖን ሰዎች ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ፥ እግዚአብሔርም ለመረጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እንጨት ቈራጮች፥ ውኃም ቀጂዎች ሆኑ።