Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 12:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 መሥዋዕትህን ሁሉ ማቅረብ የሚገባህ ከነገዶችህ መካከል የአንዱ ግዛት በሆነው ክፍል እና እግዚአብሔር በሚመርጠው በአንድ ስፍራ ብቻ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህንም ሆነ ሌላውንም እኔ ያዘዝኩህን ሁሉ በዚያ ስፍራ ብቻ ትፈጽማለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከነገዶችህ መካከል በአንዱ፣ እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ብቻ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችህን አቅርብ፤ እዚያም እኔ የማዝዝህን ሁሉ ጠብቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከነገዶችህ መካከል በአንዱ፥ ጌታ በሚመርጠው ስፍራ ብቻ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችህን አቅርብ፤ እዚያም እኔ የማዝህን ሁሉ ጠብቅ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከነ​ገ​ዶ​ችህ ከአ​ንዱ ዘንድ በመ​ረ​ጠው ስፍራ በዚያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን አቅ​ርብ፤ በዚ​ያም ዛሬ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን ሁሉ አድ​ርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ነገር ግን እግዚአብሔር ከነገዶችህ ከአንዱ ዘንድ በመረጠው ስፍራ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን አቅርብ፥ በዚያም የማዝዝህን ሁሉ አድርግ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 12:14
24 Referencias Cruzadas  

ይህም እግዚአብሔር በክርስቶስ የዓለምን ሰዎች ሁሉ ከራሱ ጋር አስታረቀ ማለት ነው፤ በደላቸውንም አልቈጠረባቸውም፤ ለእኛም ሰውን ከጌታ ጋር የምናስታርቅበትን ቃል ሰጠን።


ከዚያም እኔ ያዘዝኳችሁን ነገር ሁሉ የምታመጡት እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ መጠሪያ ወደ መረጠው ቦታ ይሆናል፤ ይኸውም የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና ሌላውንም መሥዋዕታችሁን ሁሉ፥ ዐሥራታችሁንና መባችሁን ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የተሳላችሁትን የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን ሁሉ ታመጡለታላችሁ።


አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ለእርሱ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በዚያ ስሙ እንዲጠራበት የሚመርጠውን ቦታ ፈልጉና ወደዚያ ሂዱ፤


እንግዲህ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የምስጋና መሥዋዕት ዘወትር ለእግዚአብሔር እናቅርብ፤ ይህም ስለ ስሙ በሚመሰክሩት ከንፈሮች የሚቀርብ የምስጋና መሥዋዕት ነው።


በጽዮን ለሚኖር እግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር አቅርቡ! ያደረገውንም ድንቅ ሥራ ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ!


እኔ ግን በታላቅ ምሕረትህ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ ወደ ቤተ መቅደስህ በአክብሮት እሰግዳለሁ።


የሚቃጠል መሥዋዕትህን በማናቸውም ቦታ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ።


“ሆኖም በሚያሰኛችሁ ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሰጣችሁ በረከት መሠረት ከከተሞቻችሁ በማናቸውም ቦታ ዐርዳችሁ ልትበሉ ትችላላችሁ፤ የአጋዘንና የሚዳቋ ሥጋ ለመብላት እንደሚችል ንጹሕ የሆነ ወይም ንጹሕ ያልሆነ ሰው ያን የታረደውን ሥጋ ሊበላው ይችላል።


ከእስራኤል ሕዝብ ማናቸውም ሰው በሬ፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ በሰፈር ውስጥ ወይም ከሰፈሩ ውጪ ቢያርድ፥


በተቀደሰው ስፍራ ለእግዚአብሔር ቊርባን ያቀርብ ዘንድ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ ደም በከንቱ እንዳፈሰሰ ተቈጥሮ ይፈረድበታል፤ ከሕዝቡም ይለያል።


አምላክህ እግዚአብሔር በሚመርጥልህ ቦታ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆችህ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮችህ፥ እንዲሁም በከተሞችህ ከሚኖሩ ሌዋውያን ጋር እነዚህን ትበላለህ፤ እዚያም በድካምህ ያገኘኸውን መልካም ነገር ሁሉ ትደሰትበታለህ፤


ሁልጊዜ አምላክህን እግዚአብሔርን መፍራት ትማር ዘንድ ስሙ እንዲጠራበት በሚመርጠው ቦታ የእህልህን፥ የወይን ጠጅህን፥ የዘይትህን ዐሥራት፥ እንዲሁም የከብቶችህንና የበጎችህን በኲራት በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ትበላለህ፤


እነርሱንም እግዚአብሔር በሚመርጠው ቦታ በየዓመቱ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ከቤተሰብህ ጋር ትበላቸዋለህ።


እግዚአብሔር አምላክህ ለስሙ መጠሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ እርሱን ለማክበር ከበጎችህና ከከብቶችህ መንጋዎች መርጠህ አንዳንድ ሠዋ፤


“በደም ማፍሰስ፥ በሰብአዊ መብት፥ በግድያ ወይም እነዚህን በመሳሰሉ ጉዳዮች በከተሞችህ በሚነሡ ክርክሮች የፍርድ አሰጣጡ አስቸጋሪ ቢሆንብህ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ቦታ ፈጥነህ በመሄድ


“አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከማንኛውም የእስራኤል ከተማ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ቦታ ለመምጣት ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረው፥


እስራኤላውያን ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እርሱ በሚመርጠው ቦታ በሚሰበሰቡበት ጊዜ ይህን ሕግ በፊታቸው አንብብ።


ነገር ግን በዚሁ ጊዜ እንጨት በመቊረጥና ውሃ በመቅዳት ለእስራኤል ሕዝብና ለእግዚአብሔር መሠዊያ አገልጋዮች እንዲሆኑ አደረገ። እነርሱም እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ቦታ፥ ይህንኑ አገልግሎት በመፈጸም ላይ ይገኛሉ።


እኛ በእግዚአብሔር ላይ አላመፅንም፤ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የእህል መባ፥ ወይም ሌላ መሥዋዕት ለማቅረብ አስበን ሌላ መሠዊያ በመሥራት እግዚአብሔርን ማምለክ አልተውንም፤ ከእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ለፊት ከቆመው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ከተሠራው ሌላ የተለየ መሠዊያ መሥራት ከእኛ ይራቅ።”


ስሜ ይጠራበታል ወዳልከው ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቀንና ሌሊት ተመልከት፤ እኔም አገልጋይህ ወደዚህ ቤተ መቅደስ የምጸልየውን ጸሎት ስማ።


የአሦር የጦር አዛዥ ንግግሩን በመቀጠል እንደገና እንዲህ አለ፦ “አምላክህ እግዚአብሔር እንደሚረዳህ አድርገህ ታስባለህን? ይህማ እንዳይሆን፥ አንተ የእግዚአብሔርን የተቀደሱ ስፍራዎችንና መሠዊያዎችን ደምስሰህ ‘የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ማምለክ የሚገባቸው ኢየሩሳሌም ውስጥ በሚገኘው በአንድ መሠዊያ ብቻ ነው’ ብለህ ወስነሃል።


ዳዊትም “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና የእስራኤል ሕዝብ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርቡበት መሠዊያ ሊኖሩ የሚገባቸው በዚህ ስፍራ ነው” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios