ነገር ግን ካህናቱ ጥቂቶች ነበሩና የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለመግፈፍ አይችሉም ነበር፤ ስለዚህም ሌዋውያን በቅን ልብ ከካህናት ይልቅ ይቀደሱ ነበርና ሥራው እስኪፈጸም ድረስ፥ ካህናቱም እስኪቀደሱ ድረስ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን ያግዙአቸው ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 6:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ቃል ከፍ ከፍ አለ፤ በኢየሩሳሌምም ምእመናን እጅግ በዙ፤ ከካህናትም መካከል ያመኑ ብዙዎች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፤ የደቀ መዛሙርቱም ቍጥር በኢየሩሳሌም እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙዎቹ ለእምነት የታዘዙ ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፤ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ሁኔታ የእግዚአብሔር ቃል እየተስፋፋ ስለ ሄደ፥ በኢየሩሳሌም የአማኞች ቊጥር በጣም እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም እጅግ ብዙዎቹ አመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ። |
ነገር ግን ካህናቱ ጥቂቶች ነበሩና የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለመግፈፍ አይችሉም ነበር፤ ስለዚህም ሌዋውያን በቅን ልብ ከካህናት ይልቅ ይቀደሱ ነበርና ሥራው እስኪፈጸም ድረስ፥ ካህናቱም እስኪቀደሱ ድረስ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን ያግዙአቸው ነበር።
ንጉሡ ሕዝቅያስም ስለ ቍርባን ሺህ ወይፈኖችንና ሰባት ሺህ በጎችን ለይሁዳና ለጉባኤው ሰጥቶ ነበር፤ አለቆቹም ሺህ ወይፈኖችንና ዐሥር ሺህ በጎችን ለጉባኤው ሰጥተው ነበር፤ ከካህናቱ እጅግ ብዙ ተቀድሰው ነበርና።
ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእስራኤል መካከል ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው፥ ለሚቃወሙትም ምልክት ይሆን ዘንድ የተሠየመ ነው፤
ከሕዝቡ አለቆችም ያመኑበት ብዙዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ከምኵራብ አስወጥተው እንዳይሰዱአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም።
የደቀ መዛሙርትንም ልቡና አጽናኑ፤ በሃይማኖትም እንዲጸኑ፦“ በብዙ ድካምና መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ ይገባናል” እያሉ መከሩአቸው።
እግዚአብሔርንም ያመሰግኑ ነበር፤ በሕዝቡም ሁሉ ዘንድ መወደድ ነበራቸው፤ እግዚአብሔርም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።
እነርሱም ሰምተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ እንዲህም አሉ፥ “ወንድማችን ሆይ፥ ከአይሁድ መካከል ያመኑት ስንት አእላፋት እንደ ሆኑ ታያለህን? ሁሉም ለኦሪት የሚቀኑ ናቸው።
በዚያም ወራት ደቀ መዛሙርት በበዙ ጊዜ ከግሪክ የመጡ ደቀ መዛሙርት በአይሁድ ምእመናን ላይ አንጐራጐሩባቸው፤ የዕለት የዕለቱን ምግብ ሲያካፍሉ ባልቴቶቻቸውን ቸል ይሉባቸው ነበርና።
ነገር ግን “ቀድሞ ምእመናንን ያሳድድ የነበረው እርሱ በፊት ያጠፋው የነበረውን የሃይማኖት ትምህርት ዛሬ ይሰብካል” ሲባል ወሬዬን ይሰሙ ነበር።
ይህም ወደ እናንተ የደረሰውን የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከሰማችሁበትና ከአያችሁበት ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም ያድግና ያፈራ ዘንድ ነው።
አብርሃም በተጠራ ጊዜ ርስት አድርጎ ይወርሰው ዘንድ ወዳለው ሀገር ለመሄድ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚደርስም ሳያውቅ ሄደ።
ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።