2 ሳሙኤል 7:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ታላቅ ስምን ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና ሰፈሮቻቸውን በመበተን ከግብፅ በተቤዠኸው ሕዝብህ ፊት ታምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ መራው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለራሱ ሕዝብ ይሆን ዘንድ ሊታደገው፣ እግዚአብሔር በፊቱ እንደሄደለት ሕዝብ፣ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና አማልክታቸውን ከፊቱ አሳድዶ ታላላቅና አስፈሪ ታምራት እንዳደረገለትና ከግብጽም እንደ ተቤዠው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ማን አለ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለራሱ ሕዝብ ይሆን ዘንድ ሊታደገው፥ እግዚአብሔር በፊቱ እንደሄደለት ሕዝብ፥ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና አማልክቶቻቸውን ከፊቱ አሳዶ ታላቅና አስፈሪ ታምራት እንዳደረገለትና ከግብጽም እንደ ተቤዠው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ማን አለ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ያድን ዘንድ፥ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ፥ ተአምራትንና ድንቅ ነገሮችን ያደርግ ዘንድ፥ ሕዝቦችንና አማልክቶቻቸውን በፊታቸው ያስወግድ ዘንድ እግዚአብሔር ከግብጽ ባርነት እንዳዳነው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ፥ በአሕዛብና በአምላኮቻቸውም ፊት ከግብጽ በተቤዠው ሕዝብ ፊት ተአምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ሄደለት እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ? |
አንተ እግዚአብሔር ከግብፅ ካወጣኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብን በማሳደድ ታላቅና የከበረ ስምን ለአንተ ታደርግ ዘንድ፥ ለአንተም ሕዝብ ትቤዥ ዘንድ እንደ መራኸው እንደ አንተ ሕዝብ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ የለም።
እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ ሀገር አልፋለሁ፤ በግብፅም ሀገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ በቀልን አደርግባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
በምድርም ከአለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ ተለይተን እንከብር ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልሄድህ፥ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ በእውነት ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል?” አለው።
ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፤ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
እስከ ዛሬም ድረስ ምልክትንና ድንቅን ነገር በግብፅ ምድር፥ ደግሞም በእስራኤልና በሌሎች ሰዎች መካከል አድርገሃል፤ እንደ ዛሬም ለአንተ ስም አድርገሃል።
በምልክትና በድንቅ ነገር፥ በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በታላቅም ግርማ ሕዝብህን እስራኤልን ከግብፅ ምድር አወጣህ።
ነገር ግን በመካከላቸው በአሉ፥ ከግብጽም ምድር አወጣቸው ዘንድ በፊታቸው በተገለጥሁላቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።
ዐይኖችህ ያዩአቸውን እነዚህን ታላላቆች የከበሩትን ነገሮች ያደረገልህ እርሱ መመኪያችሁ ነው፤ እርሱም አምላክህ ነው።
አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበርህ፥ አምላክህም እግዚአብሔር ከዚያ እንዳዳነህ ዐስብ፤ ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝዝሃለሁ።
እስራኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማንነው? እርሱ ያጸንሃል፤ ይረዳሃልም፤ ትምክሕትህ በሰይፍህ ነው፤ ጠላቶችህ ውሸታሞች ናቸው፤ አንተም በአንገታቸው ላይ ትጫናለህ።”
በእግዚአብሔርም ፊት እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፦ የአማልክት ንጉሥ እግዚአብሔር ሆይ፥ በታላቅ ኀይልህ የተቤዠሃቸውን፥ በጠነከረችውም እጅህና በተዘረጋች ክንድህ ከግብፅ ያወጣሃቸውን ሕዝብህንና ርስትህን አታጥፋ።
መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
ከነዓናውያንም፥ በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ሰምተው ይከብቡናል፤ ከምድርም ያጠፉናል፤ ለታላቁ ስምህም የምታደርገው ምንድር ነው?”
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።