መዝሙር 40:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ጠላቶቼም በላዬ ክፋትን ይናገራሉ፦ “መቼ ይሞታል? ስሙስ መቼ ይሻራል?” ይላሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ ያደረግኸው ድንቅ ነገር ብዙ ነው፤ ለእኛ ያቀድኸውን፣ ሊዘረዝርልህ የሚችል ማንም የለም፤ ላውራው ልናገረው ብል፣ ስፍር ቍጥር አይኖረውም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ጌታን የታመነ ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርገህልናል፤ ከአንተ የሚወዳደር ማንም የለም፤ አንተ ለእኛ ያቀድክልንን መልካም ነገር ማንም ሊቈጥረው አይችልም፤ እኔ ስለ እነርሱ በዝርዝር ለመናገርና ለማውራት ብሞክር ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ይሆንብኛል። Ver Capítulo |