በዚያም ቀን ዳዊት፥ “ኢያቡሴዎናውያንን የሚመታ ሁሉ፥ ዕውሮችንና አንካሶችን፥ የዳዊትንም ነፍስ የሚጠሉትን ሁሉ በሳንጃ ይውጋቸው” አለ። ስለዚህም፥ “ዕውርና አንካሳ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግቡ” ተባለ።
2 ሳሙኤል 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ዳዊት አንባዪቱን ጽዮንን ያዘ፤ እርስዋም የዳዊት ከተማ ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ዳዊት የጽዮንን ዐምባ ያዘ፤ ይህችም የዳዊት ከተማ የተባለችው ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁን እንጂ ዳዊት የጽዮንን ጠንካራ ምሽግ ያዘ፤ እርሷም አሁን የዳዊት ከተማ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ግን በጽዮን የሠሩትን ምሽጋቸውን ያዘ፤ እርስዋም “የዳዊት ከተማ” ተብላ ተጠራች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ዳዊት አምባይቱን ጽዮንን ያዘ፥ እርስዋም የዳዊት ከተማ ናት። |
በዚያም ቀን ዳዊት፥ “ኢያቡሴዎናውያንን የሚመታ ሁሉ፥ ዕውሮችንና አንካሶችን፥ የዳዊትንም ነፍስ የሚጠሉትን ሁሉ በሳንጃ ይውጋቸው” አለ። ስለዚህም፥ “ዕውርና አንካሳ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግቡ” ተባለ።
ዳዊትም በአንባዪቱ ውስጥ ተቀመጠ፤ እርስዋም የዳዊት ከተማ ተባለች። ከተማዋንም ዙሪያዋን እስከ ዳርቻዋ ድረስ ቀጠራት፤ ቤቱንም ሠራ።
ዳዊትም የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ ያመጣት ዘንድ አልወደደም፤ ዳዊትም በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት አገባት።
ለንጉሡ ዳዊትም “እግዚአብሔር የአቢዳራን ቤትና የነበረውን ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገሩት። ዳዊትም ሄዶ የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደስታ አመጣት።
የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰች ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልልና ሲዘምር አየችው፥ በልብዋም ናቀችው።
ሰሎሞንም ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን አማች ሆነ፤ የፈርዖንንም ልጅ አገባ፤ ቤቱንና የእግዚአብሔርንም ቤት፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ያለውን ቅጥር ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አምጥቶ አስገባት።
ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤተ መንግሥት ሠርቶ ከፈጸመ ከሃያ ዓመት በኋላ ያንጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች የአባቶቻቸውን ቤቶች መሳፍንት ንጉሡ ሰሎሞን በጽዮን ሰበሰባቸው።
በዚያ ጊዜም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ፥ የእስራኤልንም ልጆች አባቶች ቤቶች መሳፍንት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
የመሴፋም ገዢ የኮልሐዜ ልጅ ሰሎም የምንጩን በር አደሰ፤ ሠራው፤ ከደነውም፤ ሳንቃዎቹንም አቆመ፤ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ፤ ከዳዊትም ከተማ እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ያለውን የመዋኛ ቅጥር ሠራ።
እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድንጋያማ ሸለቆ የምትቀመጥ ሆይ! እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤ እናንተም፦ የሚያስደነግጠን ወይም ወደ መኖሪያችን የሚገባ ማን ነው? የምትሉ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፤
ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።
መጽሐፍ እንዲሁ “በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይንና የማሰናከያ ዐለትን አኖራለሁ፤ ያመነባትም ለዘለዓለም አያፍርም” ብሎአልና።
እናንተ ግን፥ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደምትሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰማያት ወደ አለችው ኢየሩሳሌም፥ ደስ ብሎአቸው ወደሚኖሩ አእላፍ መላእክትም ደርሳችኋል።