Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በዚያ ጊዜም ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳ​ዊት ከተማ ከጽ​ዮን ያወጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የነ​ገድ አለ​ቆ​ችን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች አባ​ቶች ቤቶች መሳ​ፍ​ንት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከዚያም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን እንዲያመጡ፣ የእስራኤልን ሽማግሌዎች፣ የእስራኤልን ነገድ አለቆችና የእስራኤልን ጐሣዎች ሹማምት ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበሰበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በዚያን ጊዜም ሰሎሞን የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን እንዲያመጡ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ የእስራኤልንም ልጆች አባቶች ቤቶች መሳፍንት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን ወደ ቤተ መቅደሱ ያመጡ ዘንድ የእስራኤል ሽማግሌዎች፥ የነገድና የቤተሰብ አለቆች ሁሉ በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ትእዛዝ ሰጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በዚያን ጊዜም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያመጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ የእስራኤልንም ልጆች አባቶች ቤቶች መሳፍንት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 5:2
21 Referencias Cruzadas  

ለን​ጉሡ ዳዊ​ትም “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ቢ​ዳ​ራን ቤትና የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገ​ሩት። ዳዊ​ትም ሄዶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከአ​ቢ​ዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ስታ አመ​ጣት።


ዳዊት ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም አወ​ጣት። ለእ​ርሷ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ድን​ኳን አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላት ነበ​ርና።


ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥ ጆሮ​ህ​ንም ወደ ልመ​ናዬ አዘ​ን​ብል፤


እኔ ግን በእ​ነ​ርሱ ላይ ንጉሥ ሆኜ ተሾ​ምሁ በተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራው በጽ​ዮን ላይ።


መዘ​ም​ራ​ንም የነ​በ​ሩት ሌዋ​ው​ያን ሁሉ፥ ከአ​ሳ​ፍና ከኤ​ማን፥ ከኤ​ዶ​ት​ምም ልጆች ጋር ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ ጥሩ በፍታ ለብ​ሰው ጸና​ጽ​ልና ከበሮ፥ መሰ​ን​ቆም እየ​መቱ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በም​ሥ​ራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር መቶ ሃያ ካህ​ናት መለ​ከት ይነፉ ነበር።


ሰሎ​ሞ​ንም አባቱ ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ የመ​ገ​ል​ገያ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ አም​ጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በ​ረው ግምጃ ቤት አገባ።


ዳዊ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አለ​ቆች ሁሉና የፍ​ርድ አለ​ቆ​ችን፥ ንጉ​ሡ​ንም በየ​ተራ የሚ​ጠ​ብ​ቁ​ትን አለ​ቆ​ቹን፥ ሻለ​ቆ​ቹ​ንም፥ የመቶ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ በን​ጉ​ሡና በል​ጆቹ ሀብ​ትና ንብ​ረት ላይ፥ መባ ባለ​በት ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን ጃን​ደ​ረ​ቦ​ች​ንም፥ ኀያ​ላ​ኑ​ንና ሰል​ፈ​ኞ​ቹን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።


ይህ ሰሎ​ሚ​ትና ወን​ድ​ሞቹ፥ ንጉሡ ዳዊ​ትና የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች፥ ሻለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለ​ቆች፥ በቀ​ደ​ሱት በን​ዋየ ቅድ​ሳቱ ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ ላይ ተሹ​መው ነበር።


እነ​ዚ​ህም ደግሞ በን​ጉሡ በዳ​ዊ​ትና በሳ​ዶቅ በአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም በሌ​ዋ​ው​ያ​ንና በካ​ህ​ናት አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት፥ ታላ​ላ​ቆች እንደ ታና​ናሽ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣ​ጣሉ።


ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገን የነ​በ​ረው የና​ት​ና​ኤል ልጅ ጸሓ​ፊው ሳም​ያስ በን​ጉ​ሡና በአ​ለ​ቆቹ ፊት ፥ በካ​ህኑ በሳ​ዶ​ቅና በአ​ብ​ያ​ታ​ርም ልጅ በአ​ቤ​ሜ​ሌክ ፊት ፥ በካ​ህ​ና​ቱና በሌ​ዋ​ው​ያኑ አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት ጻፋ​ቸው፤ አን​ዱ​ንም የአ​ባት ቤት ለአ​ል​ዓ​ዛር፥ አን​ዱ​ንም ለኢ​ታ​ምር ጻፈ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ይዘው ገቡ፤ ዳዊ​ትም በተ​ከ​ለ​ላት ድን​ኳን ውስጥ አኖ​ሩ​አት፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረቡ።


ዳዊ​ትም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ የሻ​ለ​ቆ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ከአ​ቢ​ዳራ ቤት በደ​ስታ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።


“እና​ንተ የሌ​ዋ​ው​ያን አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ናችሁ፤ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላት ስፍራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ታመጡ ዘንድ እና​ን​ተና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ተቀ​ደሱ።


ነገር ግን ዳዊት አን​ባ​ዪ​ቱን ጽዮ​ንን ያዘ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ናት።


ከሰ​ፈ​ራ​ቸ​ውም በተ​ጓዙ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደመና ቀን ቀን በላ​ያ​ቸው ላይ ነበረ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተራራ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ያህል ተጓዙ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የኪ​ዳኑ ታቦት የሚ​ያ​ድ​ሩ​በ​ትን ቦታ ታገ​ኝ​ላ​ቸው ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ትቀ​ድ​ማ​ቸው ነበር።


ሙሴም ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ቀር​በው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ።


ዳዊ​ትም በከ​ተ​ማው ለራሱ ቤቶ​ችን ሠራ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ስፍራ አዘ​ጋጀ፤ ድን​ኳ​ንም ተከ​ለ​ላት።


ዳዊ​ትም ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ላት ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios