Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የመ​ሴ​ፋም ገዢ የኮ​ል​ሐዜ ልጅ ሰሎም የም​ን​ጩን በር አደሰ፤ ሠራው፤ ከደ​ነ​ውም፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ፤ ከዳ​ዊ​ትም ከተማ እስ​ከ​ሚ​ወ​ር​ደው ደረጃ ድረስ በን​ጉሡ አት​ክ​ልት አጠ​ገብ ያለ​ውን የመ​ዋኛ ቅጥር ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የምጽጳ አውራጃ አለቃ የኮልሖዜ ልጅ ሰሎም “የምንጭ በር” ተብሎ የሚጠራውን መልሶ ሠራ፤ መልሶ ከሠራም በኋላ ከድኖ መዝጊያዎቹን በየቦታቸው አኖረ፤ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹንም አበጀ። የንጉሥ አትክልት ቦታ ተብሎ በሚጠራው አጠገብ የሚገኘውን የሼላን መዋኛ ግንብም፣ ከዳዊት ከተማ ጀምሮ ቍልቍል እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ መልሶ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የሚጽጳም አውራጃ ገዢ የኮልሖዜ ልጅ ሻሉን “የምንጭ በር” አደሰ፤ መልሶ ሠራው፥ ከደነውም፥ በሮቹን አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጀ፤ በንጉሡ አትክልት ቦታ አጠገብ ያለውን የሼላሕን መዋኛ ቅጥር ከዳዊት ከተማ ወደ ታች እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የምጽጳ ወረዳ ገዢ የሆነው የኮልሖዜ ልጅ ሻሉም የምንጩን ቅጽር በር እንደገና ሠራ፤ ክዳን ከሠራለትም በኋላ መዝጊያዎችን አቆመ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጀ፤ በሼላሕ ኩሬ ቅጥር በኩል ከቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ጀምሮ ከዳዊት ከተማ ወደታች እስከሚያወርደው ደረጃ ድረስ ያለውን ክፍል እንደገና ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የምጽጳም ግዛት አለቃ የኮልሖዜ ልጅ ሰሎም የምንጩን በር አደሰ፥ ሠራው፥ ከደነውም፥ ሳንቃዎቹንም አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ፥ ከዳዊትም ከተማ እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ያለውን የሼላን መዋኛ ቅጥር ሠራ።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 3:15
19 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሂድና በሰ​ሊ​ሆም መጠ​መ​ቂያ ታጠብ” ትር​ጓ​ሜ​ውም የተ​ላከ ማለት ነው፤ ሄዶም ታጠ​በና እያየ ተመ​ለሰ።


“እኒህ ሕዝብ በቀ​ስታ በሚ​ሄ​ደው በሰ​ሊ​ሆም ውኃ ቍርጥ ምክ​ርን መከሩ፤ ረአ​ሶ​ን​ንና የሮ​ሜ​ል​ዩን ልጅ ያነ​ግ​ሡ​ላ​ቸው ዘንድ ይወ​ዳ​ሉና።


በም​ን​ጭም በር አቅ​ን​ተው ሄዱ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ደረጃ፥ በቅ​ጥ​ሩም መውጫ፥ ከዳ​ዊ​ትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል ሄዱ።


ወይስ እነ​ዚያ በሰ​ሊ​ሆም ግንብ ተጭኖ የገ​ደ​ላ​ቸው ዐሥራ ስም​ንቱ ሰዎች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰዎች ይልቅ ተለ​ይ​ተው ኀጢ​እ​ታ​ኞች ይመ​ስ​ሉ​አ​ች​ኋ​ልን?


ወደ ምን​ጩም በርና ወደ ንጉ​ሡም መዋኛ አለ​ፍሁ፤ ተቀ​ም​ጬ​በት የነ​በ​ረው እን​ስ​ሳም የሚ​ያ​ል​ፍ​በት ስፍራ አል​ነ​በ​ረም።


ኤር​ም​ያ​ስም የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ወደ አለ​በት ወደ መሴፋ ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር በሀ​ገሩ ውስጥ በቀ​ሩት ሕዝብ መካ​ከል ተቀ​መጠ።


የቤ​ት​ሐ​ካ​ሪ​ምም ግዛት ገዢ የሬ​ካብ ልጅ መል​ክያ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹና ከል​ጆቹ ጋር የጕ​ድፍ መጣ​ያ​ውን በር ሠራ፤ ከደ​ነው፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ።


በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ግዛት እኩ​ሌታ ገዢ የአ​ሎ​ኤስ ልጅ ሰሎ​ምና ሴቶች ልጆቹ ሠሩ።


በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ግዛት እኩ​ሌታ አለቃ የሆር ልጅ ረፋያ ሠራ።


በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ገባ​ዖ​ና​ዊው መል​ጥ​ያና ሜሮ​ና​ታ​ዊው ያዴን፥ እስከ ወን​ዙም ማዶ አለቃ ግዛት የሆኑ የገ​ባ​ዖ​ንና የመ​ሴፋ ሰዎች ሠሩ።


ይህም ሕዝ​ቅ​ያስ የላ​ይ​ኛ​ውን የግ​ዮ​ንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ በም​ዕ​ራብ በኩል አቅ​ንቶ አወ​ረ​ደው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በሥ​ራው ሁሉ ተከ​ና​ወነ።


ከተ​ማ​ዪ​ቱም ተሰ​በ​ረች፤ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ሁሉ በሁ​ለት ቅጥር መካ​ከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አት​ክ​ልት በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ በሌ​ሊት ሸሹ፤ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ ወደ ምድረ በዳ በሚ​ወ​ስ​ደ​ውም መን​ገድ ሄዱ።


የብ​ን​ያ​ምም ልጆች የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ወጡ ሰሙ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “ይህ ክፉ ነገር እን​ደ​ምን እንደ ተደ​ረገ ንገ​ሩን” አሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ፥ ከገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።


እኔም፥ “እኛ ያለ​ን​በ​ትን ጕስ​ቍ​ልና፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ፈረ​ሰች፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት እንደ ተቃ​ጠሉ ታያ​ላ​ችሁ። አሁ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ መሳ​ለ​ቂያ እን​ዳ​ን​ሆን ኑና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅጥር እን​ሥራ” አል​ኋ​ቸው።


በአ​ጠ​ገ​ቡም የመ​ሴፋ ገዢ የኢ​ያሱ ልጅ አዙር በማ​ዕ​ዘኑ አጠ​ገብ በመ​ወ​ጣ​ጫው ግንብ አን​ጻር ያለ​ውን ሌላ​ውን ክፍል ሠራ።


የሚ​ያ​ፈራ እን​ጨ​ት​ንና የተ​ተ​ከ​ሉ​ትን ዛፎች አጠ​ጣ​በት ዘንድ የውኃ ማጠ​ራ​ቀ​ሚ​ያን አደ​ረ​ግሁ።


ዳዊ​ትም በአ​ን​ባ​ዪቱ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ተባ​ለች። ከተ​ማ​ዋ​ንም ዙሪ​ያ​ዋን እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ቀጠ​ራት፤ ቤቱ​ንም ሠራ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios