Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 9:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 መጽ​ሐፍ እን​ዲሁ “በጽ​ዮን የእ​ን​ቅ​ፋት ድን​ጋ​ይ​ንና የማ​ሰ​ና​ከያ ዐለ​ትን አኖ​ራ​ለሁ፤ ያመ​ነ​ባ​ትም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ፍ​ርም” ብሎ​አ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ይህም፣ “እነሆ፤ የሚያደናቅፍ ድንጋይ፣ የሚጥልም ዐለት፣ በጽዮን አስቀምጣለሁ፤ በርሱም የሚያምን አያፍርም” ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ይህም “እነሆ፥ በጽዮን የሚያደናቅፍ ድንጋይና የሚያሰናክል ዓለት አኖራለሁ፥ በእርሱም የሚያምን አያፍርም” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ይህም፦ “እነሆ፥ ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ ይህም ድንጋይ ሰዎችን በማሰናከል የሚጥል አለት ነው፤ በእርሱ የሚያምን ግን አያፍርም” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 9:33
19 Referencias Cruzadas  

ትእ​ዛ​ዝ​ህን ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና ስድ​ብ​ንና ነው​ርን ከእኔ አርቅ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በጽ​ዮን ድን​ጋ​ይን ለመ​ሠ​ረት አስ​ቀ​ም​ጣ​ለሁ፤ ዋጋው ብዙ የሆ​ነ​ውን፥ የተ​መ​ረ​ጠ​ውን፥ የከ​በ​ረ​ው​ንና መሠ​ረቱ የጸ​ና​ውን የማ​ዕ​ዘን ድን​ጋይ አኖ​ራ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም የሚ​ያ​ምን አያ​ፍ​ርም።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን በዘ​ለ​ዓ​ለ​ማዊ መድ​ኀ​ኒት ያድ​ነ​ዋል፤ እና​ን​ተም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ፍ​ሩ​ምና አቷ​ረ​ዱም።”


አታ​ፍ​ሪ​ምና አት​ፍሪ፤ አቷ​ረ​ጂ​ምና አት​ደ​ን​ግጪ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም እፍ​ረ​ት​ሽ​ንም ትረ​ሺ​ዋ​ለሽ፤ የመ​በ​ለ​ት​ነ​ት​ሽ​ንም ስድብ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አታ​ስ​ቢም።


ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?


በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩ ግን የሚወድቅበትን ሁሉ ይፈጨዋል።”


ወን​ድ​ሞች፥ የእ​ኔስ የልቤ ምኞት፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የማ​ቀ​ር​በው ጸሎ​ትም እስ​ራ​ኤል እን​ዲ​ድኑ ነው።


መጽ​ሐፍ፥ “የሚ​ያ​ም​ን​በት ሁሉ አያ​ፍ​ርም” ብሎ​አል።


ተስ​ፋም አያ​ሳ​ፍ​ርም፤ በሰ​ጠን በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቅር በል​ባ​ችን መል​ቶ​አ​ልና።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔ ግዝ​ረ​ትን ገና የም​ሰ​ብክ ከሆነ፥ እን​ግ​ዲህ ለምን ያሳ​ድ​ዱ​ኛል? እን​ግ​ዲህ የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ተግ​ዳ​ሮት እን​ዲ​ያው ቀር​ቶ​አል።


በም​ንም እን​ደ​ማ​ላ​ፍር ተስፋ እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና እን​ደ​ታ​መ​ንሁ እንደ ወት​ሮው በልብ ደስታ በግ​ል​ጥ​ነት፥ አሁ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ክብር በሕ​ይ​ወ​ቴም ቢሆን፥ በሞ​ቴም ቢሆን በሰ​ው​ነቴ ይገ​ለ​ጣል።


ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፤ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።


አሁንም፥ ልጆች ሆይ፥ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos