La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 19:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዛሬ የሰ​ማ​ንያ ዓመት ሽማ​ግሌ ነኝ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን መለ​የት እች​ላ​ለ​ሁን? እኔ ባሪ​ያህ የም​በ​ላ​ው​ንና የም​ጠ​ጣ​ውን ጣዕ​ሙን መለ​የት እች​ላ​ለ​ሁን? የወ​ን​ዱ​ንና የሴ​ቲ​ቱን ዘፈን ድምፅ መስ​ማ​ትስ እች​ላ​ለ​ሁን? እኔ ባሪ​ያህ በጌ​ታዬ በን​ጉሡ ላይ ለምን እከ​ብ​ድ​ብ​ሃ​ለሁ?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነኝ፤ ታዲያ ደግና ክፉውን መለየት እችላለሁ? ከእንግዲህ አገልጋይህ የሚበላውንና የሚጠጣውን ጣዕሙን መለየት ይችላል? የሚዘፍኑትን የወንዶችና የሴቶችን ድምፅ አሁንም መስማት እችላለሁ? ታዲያ አገልጋይህ ለንጉሥ ጌታዬ ለምን ተጨማሪ ሸክም ይሆናል?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ባርዚላይ ግን ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ከንጉሡ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የምሄደው ለየትኛው ዕድሜዬ ብዬ ነው?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነሆ፥ እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሰው ነኝ፤ የሚያስደስቱና የማያስደስቱ ነገሮችን መለየት እችላለሁን? የምበላውንም ሆነ የምጠጣውን ጣዕም መለየት እችላለሁን? ጆሮዬም የወንድና የሴት ዘፋኞችን ድምፅ መስማት ይችላልን? ንጉሥ ሆይ! በጌታዬ ላይ ለምን ተጨማሪ ሸክም እሆንብሃለሁ?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዛሬ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነኝ፥ መልካሙንና ክፉውን መለየት እችላለሁን? እኔ ባሪያህ የምበላውንና የምጠጣውን ጣዕሙን መለየት እችላለሁን? የወንዱንና የሴቲቱን ዘፈን ድምፅ መስማት እችላለሁን? እኔ ባሪያህ በጌታዬ በንጉሡ ላይ ለምን እከብድብሃለሁ?

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 19:35
15 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “ልጄ ሆይ፥ አይ​ሆ​ንም፤ እን​ከ​ብ​ድ​ብ​ሃ​ለ​ንና ሁላ​ችን አን​ሄ​ድም” አለው። የግ​ድም አለው፤ እርሱ ግን መረ​ቀው እንጂ ለመ​ሄድ እንቢ አለ።


ዳዊ​ትም አለው፥ “ከእኔ ጋር ብት​ሻ​ገር ሸክም ትሆ​ን​ብ​ኛ​ለህ፤


እኔ ባሪ​ያህ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግሬ ከን​ጉሡ ጋር ጥቂት ልሄድ ነበር፤ ንጉሡ እን​ዲህ ያለ ወረታ ለምን ይመ​ል​ስ​ል​ኛል?


ይኸ​ውም ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነ​በሩ ከሎ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውና ከገ​ረ​ዶ​ቻ​ቸው ሌላ ሁለት መቶ ወን​ዶች መዘ​ም​ራ​ንና ሴቶች መዘ​ም​ራ​ትም ነበ​ሩ​አ​ቸው።


ይኸ​ውም ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነ​በሩ ከሎ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውና ከገ​ረ​ዶ​ቻ​ቸው ሌላ ሁለት መቶም አርባ አም​ስት ወን​ዶች መዘ​ም​ራ​ንና ሴቶች መዘ​ም​ራት ነበ​ሩ​አ​ቸው።


ዦሮ ነገ​ርን የሚ​ለይ አይ​ደ​ለ​ምን? ጕረ​ሮስ መብ​ልን የሚ​ቀ​ምስ አይ​ደ​ለ​ምን?


በአ​ን​ደ​በቴ በደል የለ​ምና አፌ ጕሮ​ሮ​ዬም ጥበ​ብን ይና​ገ​ራል።


ክፉ ነገር ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ብም፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ወደ ቤትህ አይ​ገ​ባም።


በቤት ያሉት ሰዎች ጥቂት ቢሆኑ፥ አንድ በግም የማ​ይ​ጨ​ርሱ ቢሆኑ በጉን ሊጨ​ርሱ በሚ​በቁ በሰ​ዎች ቍጥር እያ​ን​ዳ​ንዱ በአ​ጠ​ገቡ የሚ​ኖ​ረ​ውን ጎረ​ቤ​ቱን ይው​ሰድ።


የፈ​ር​ዖ​ንም ልጅ፥ “ሂጂና ጥሪ​ልኝ” አለ​ቻት፤ ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም ሄዳ የሕ​ፃ​ኑን እናት ጠራች።


ብር​ንና ወር​ቅን፥ የከ​በ​ረ​ው​ንም የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንና የአ​ው​ራ​ጆ​ችን መዝ​ገብ ለራሴ ሰበ​ሰ​ብሁ፤ ሴቶ​ችና ወን​ዶች አዝ​ማ​ሪ​ዎ​ችን፥ የሰ​ዎች ልጆ​ች​ንም ተድላ አደ​ረ​ግሁ፤ የወ​ይን ጠጅ ጠማ​ቂ​ዎ​ች​ንና አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ች​ንም አበ​ዛሁ።


ጠን​ካራ ምግብ ግን መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ዉን ለመ​ለ​የት በሥ​ራ​ቸው የለ​መደ ልቡና ላላ​ቸው ለፍ​ጹ​ማን ሰዎች ነው።