Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 19:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 እነሆ፥ እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሰው ነኝ፤ የሚያስደስቱና የማያስደስቱ ነገሮችን መለየት እችላለሁን? የምበላውንም ሆነ የምጠጣውን ጣዕም መለየት እችላለሁን? ጆሮዬም የወንድና የሴት ዘፋኞችን ድምፅ መስማት ይችላልን? ንጉሥ ሆይ! በጌታዬ ላይ ለምን ተጨማሪ ሸክም እሆንብሃለሁ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነኝ፤ ታዲያ ደግና ክፉውን መለየት እችላለሁ? ከእንግዲህ አገልጋይህ የሚበላውንና የሚጠጣውን ጣዕሙን መለየት ይችላል? የሚዘፍኑትን የወንዶችና የሴቶችን ድምፅ አሁንም መስማት እችላለሁ? ታዲያ አገልጋይህ ለንጉሥ ጌታዬ ለምን ተጨማሪ ሸክም ይሆናል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ባርዚላይ ግን ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ከንጉሡ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የምሄደው ለየትኛው ዕድሜዬ ብዬ ነው?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ዛሬ የሰ​ማ​ንያ ዓመት ሽማ​ግሌ ነኝ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን መለ​የት እች​ላ​ለ​ሁን? እኔ ባሪ​ያህ የም​በ​ላ​ው​ንና የም​ጠ​ጣ​ውን ጣዕ​ሙን መለ​የት እች​ላ​ለ​ሁን? የወ​ን​ዱ​ንና የሴ​ቲ​ቱን ዘፈን ድምፅ መስ​ማ​ትስ እች​ላ​ለ​ሁን? እኔ ባሪ​ያህ በጌ​ታዬ በን​ጉሡ ላይ ለምን እከ​ብ​ድ​ብ​ሃ​ለሁ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ዛሬ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነኝ፥ መልካሙንና ክፉውን መለየት እችላለሁን? እኔ ባሪያህ የምበላውንና የምጠጣውን ጣዕሙን መለየት እችላለሁን? የወንዱንና የሴቲቱን ዘፈን ድምፅ መስማት እችላለሁን? እኔ ባሪያህ በጌታዬ በንጉሡ ላይ ለምን እከብድብሃለሁ?

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 19:35
15 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም “ልጄ ሆይ! መምጣት አያስፈልገንም፤ እኛ ሁላችን ከመጣን መስተንግዶው ይከብድብሃል” ሲል መለሰለት፤ አቤሴሎምም አጥብቆ ጠየቀ፤ ንጉሡ ግን አሳቡን መለወጥ ስላልፈቀደ አቤሴሎምን መርቆ አሰናበተው።


ዳዊትም እንዲህ አለው፦ “አንተ እኔን ተከትለህ ብትሄድ ወደ ኋላ ትጐትተናለህ፤


ደግሞም ንጉሡ ይህን ያኽል ታላቅ ወሮታ የሚከፍለኝ ለምንድን ነው? ነገር ግን የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሬ ከአንተ ጋር ጥቂት መንገድ ብቻ እሄዳለሁ።


ምላስ የምግብን ጣዕም ለይቶ እንደሚያውቅ፥ ጆሮም የንግግርን ዐይነት መርምሮ ይለያል።


በውኑ በአንደበቴ በደል ይገኛልን? አፌስ ተንኰልን ይለይ ዘንድ አይችልምን?


ዕድሜአችን ሰባ ዓመት ነው፤ ቢበዛም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ እነዚያም ዘመናት በችግርና በሐዘን የተሞሉ ናቸው፤ ዕድሜአችን በቶሎ ያልቃል፤ እኛም እናልፋለን።


ቤተሰቡ አነስተኛ ከመሆኑ የተነሣ እንስሳውን በልቶ ለመጨረስ የማይችል ከሆነ ግን እርሱና የቅርብ ጐረቤቱ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ሊመገበው የሚችለውን ያኽል ተመጥኖ እንስሳውን በአንድነት አብረው ይብሉት።


“አዎ፥ ሄደሽ ጥሪልኝ” ስላለቻት ልጅቱ ሄደች፤ የሕፃኑንም እናት ጠርታ አመጣች።


እኔ በምገዛው አገር ሁሉ ከልዩ ልዩ አውራጃዎች የከበሩ የቤተ መንግሥት መዛግብትን በመሰብሰብ ብዙ ወርቅና ብር አከማቸሁ፤ እኔን የሚያሞግሡ ወንዶችና ሴቶች አዝማሪዎችንም አዘጋጀሁ፤ ለሰው ተድላና ደስታን ሊሰጡ የሚችሉ እጅግ ብዙ ሴቶችንም ሰበሰብኩ።


ጠንካራ ምግብ የሚያስፈልጋቸው ግን መልካሙንና ክፉውን የመለየት ልምድ ያላቸው ትላልቅ ሰዎች ናቸው።


ልትመኙ የምትችሉትም “ጌታ ለጋስ መሆኑን ዐውቃችሁ እንደ ሆነ ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos