Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 5:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ጠን​ካራ ምግብ ግን መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ዉን ለመ​ለ​የት በሥ​ራ​ቸው የለ​መደ ልቡና ላላ​ቸው ለፍ​ጹ​ማን ሰዎች ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙን ከክፉው ለመለየት ራሳቸውን ላስለመዱ፣ ለበሰሉ ሰዎች ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጠንካራ ምግብ የሚያስፈልጋቸው ግን መልካሙንና ክፉውን የመለየት ልምድ ያላቸው ብስለት ያላቸው ሰዎች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ጠንካራ ምግብ የሚያስፈልጋቸው ግን መልካሙንና ክፉውን የመለየት ልምድ ያላቸው ትላልቅ ሰዎች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 5:14
24 Referencias Cruzadas  

ከእ​ር​ስዋ በበ​ላ​ችሁ ቀን፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ እን​ዲ​ከ​ፈቱ፥ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ም​ት​ሆኑ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን እን​ደ​ም​ታ​ውቁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ሚ​ያ​ውቅ ነው እንጂ።”


ያችም ሴት አለች፥ “መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን ነገር ለመ​ስ​ማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ መሥ​ዋ​ዕ​ትና እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ነውና የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ቃል እን​ደ​ዚሁ ነው፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ይሁን።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ፍር​ድን ትለይ ዘንድ ለራ​ስህ ማስ​ተ​ዋ​ልን ለመ​ንህ እንጂ ለራ​ስህ ብዙ ዘመ​ና​ትን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ንም፥ የጠ​ላ​ቶ​ች​ህ​ንም ነፍስ ሳት​ለ​ምን ይህን ነገር ለም​ነ​ሃ​ልና፥


ስለ​ዚ​ህም ሰምቶ በሕ​ዝ​ብህ ላይ መፍ​ረድ ይችል ዘንድ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ው​ንም ይለይ ዘንድ ለባ​ሪ​ያህ አስ​ተ​ዋይ ልቡና ስጠው፤ አለ​ዚ​ያማ በዚህ በታ​ላቅ ሕዝብ ላይ ይፈ​ርድ ዘንድ ማን ይች​ላል?”


ዦሮ ነገ​ርን የሚ​ለይ አይ​ደ​ለ​ምን? ጕረ​ሮስ መብ​ልን የሚ​ቀ​ምስ አይ​ደ​ለ​ምን?


ጆሮ ቃልን ትለ​ያ​ለ​ችና፥ ጕሮ​ሮም የመ​ብ​ልን ጣዕም ይለ​ያል።


በአ​ን​ደ​በቴ በደል የለ​ምና አፌ ጕሮ​ሮ​ዬም ጥበ​ብን ይና​ገ​ራል።


የሽ​ቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥ ስምህ እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ሽቱ ነው፤ ስለ​ዚህ ደና​ግል ወደ​ዱህ።


በዱር እን​ዳለ እን​ኮይ፥ እን​ዲሁ ውዴ በወ​ን​ድ​ሞች መካ​ከል ነው። ከጥ​ላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀ​መ​ጥሁ፥ ፍሬ​ውም ለጕ​ሮ​ሮዬ ጣፋጭ ነው።


ሕፃኑ ክፉን ለመ​ጥ​ላት መል​ካ​ሙ​ንም ለመ​ም​ረጥ ሳያ​ውቅ ቅቤና ማር ይበ​ላል።


እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።


እም​ነቱ ደካማ የሆ​ነ​ውን ሰው ታገ​ሡት፤ በዐ​ሳ​ቡም አት​ፍ​ረዱ።


ለዐ​ዋ​ቆች ጥበ​ብን እን​ነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለን፤ ነገር ግን የዚ​ህን ዓለም ጥበብ ወይም ያልፉ ዘንድ ያላ​ቸ​ውን የዚ​ህን ዓለም ሹሞች ጥበብ አይ​ደ​ለም።


ዐይነ ልቡ​ና​ች​ሁ​ንም ያበ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ፥ የተ​ጠ​ራ​ች​ሁ​በት ተስ​ፋም ምን እንደ ሆነ፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንም የር​ስቱ ክብር ባለ​ጸ​ግ​ነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ፥


ሁላ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ በማ​መ​ንና በማ​ወቅ አንድ እስ​ክ​ን​ሆን ድረስ በክ​ር​ስ​ቶስ ምል​ዐት መጠን፥ አካለ መጠን እንደ አደ​ረሰ እንደ አንድ ሙሉ ሰው እስ​ክ​ን​ሆን ድረስ፥


ፍጹ​ማን የሆ​ና​ችሁ ሁላ​ችሁ ይህን አስቡ፤ ሌላ የም​ታ​ስ​ቡት ቢኖ​ርም፥ እር​ሱን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ል​ጥ​ላ​ች​ኋል።


ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።


ስለ​ዚ​ህም የክ​ር​ስ​ቶ​ስን የነ​ገ​ሩን መጀ​መ​ሪያ ትተን ወደ ፍጻ​ሜው እን​ሂድ፤ እን​ግ​ዲህ ደግሞ ሌላ መሠ​ረት እን​ዳ​ትሹ ዕወቁ፤ ይኸ​ውም ከሞት ሥራ ለመ​መ​ለስ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለማ​መን፥


ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos