2 ነገሥት 2:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘወርም ብሎ አያቸው፤ በእግዚአብሔርም ስም ረገማቸው፤ ወዲያውም ከዱር ሁለት ድቦች ወጥተው ከእነርሱ አርባ ሁለቱን ሰባበሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልሳዕም ዘወር ብሎ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ ከዚያም ሁለት እንስት ድቦች ከዱር ወጥተው ከልጆቹ አርባ ሁለቱን ሰባበሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት፥ አተኲሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት፥ አተኲሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘወርም ብሎ አያቸው፤ በእግዚአብሔርም ስም ረገማቸው፤ ከዱርም ሁለት ድቦች ወጥተው ከብላቴኖች አርባ ሁለቱን ሰባበሩአቸው። |
ኩሲ ደግሞ አለ፥ “በሜዳ እንዳለች አራስ ድብና እንደ ተኳር የዱር እሪያ በልባቸው መራሮችና ኀያላን መሆናቸውን አባትህንና ሰዎቹን ታውቃለህ፤ አባትህ አርበኛ ነው፤ ሕዝቡንም አያሰናብትም።
ተነሥቶም ሄደ፤ በመንገዱም ላይ አንበሳ አግኝቶ ገደለው፤ ሬሳውም በመንገድ ላይ ተጋድሞ ነበር፤ አህያውም በእርሱ አጠገብ ቆሞ ነበር፤ አንበሳውም ደግሞ በሬሳው አጠገብ ቆሞ ነበር።
ከአዛሄልም ሰይፍ የሚያመልጠውን ሁሉ ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ የሚያመልጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል።
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ከገጸ ምድር አስወግድሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ዐመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ” አለው።
በአሦራውያንም መንገድ አጠገብ እንደ ተራበ ድብ እገጥማቸዋለሁ፤ የልባቸውንም ሥር እቈርጣለሁ፤ በዚያም የዱር አንበሶች ይበሏቸዋል፤ የምድረ በዳም አራዊት ይነጣጠቋቸዋል።
በእናንተ ላይ ክፉዎች የምድርን አራዊት እሰድዳለሁ፤ ይበሉአችኋል፤ እንስሶቻችሁንም ያጠፋሉ፤ እናንተንም ያሳንሳሉ፤ መንገዶቻችሁም በረሃ ይሆናሉ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ አመንዝራ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም በገመድ ትከፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።”
ጴጥሮስም፥ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን መንፈስ ትፈታተኑት ዘንድ እንዴት ተባበራችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግሮች በበር ናቸው፤ አንቺንም ይወስዱሻል” አላት።
እንዲህ ባይሆን ግን ከአቤሜሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰቂማንም ሰዎች፥ የመሐሎንንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይሆን ከሰቂማ ሰዎች ከመሐሎንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤሜሌክንም ትብላው።”
እግዚአብሔርም የሰቂማን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰባቸው፤ የይሩበኣል ልጅ የኢዮአታምም ርግማን ደረሰባቸው።