Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 9:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ኖኅም እን​ዲህ አለ፥ “ከነ​ዓን ርጉም ይሁን፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የባ​ሪ​ያ​ዎች ባሪያ ይሁን።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እንዲህም አለ፤ “ከነዓን የተረገመ ይሁን፤ ለወንድሞቹም፣ የባሪያ ባሪያ ይሁን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እንዲህም አለ፦ “ከነዓን የተረገመ ይሁን! ለወንድሞቹም የባርያዎች ባርያ ይሁን።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እንዲህም አለ፤ “ከነዓን የተረገመ ይሁን! ለወንድሞቹ የአገልጋዮች አገልጋይ ይሁን፤ እንደገናም እንዲህ አለ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እንዲህም አለ፥ ከነዓን ርጉም ይሁን ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 9:25
15 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም የተ​ረ​ገ​ማ​ችሁ ሁኑ፤ ለእ​ኔም፥ ለአ​ም​ላ​ኬም እን​ጨት ቈራጭ፥ ውኃም ቀጂ የሆነ ባሪያ ከእ​ና​ንተ አይ​ጠ​ፋም” አላ​ቸው።


“አባ​ቱን ወይም እና​ቱን የሚ​ያ​ቃ​ልል ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ኀጢ​ኣ​ትን የሚ​ሠራ ሁሉ የኀ​ጢ​ኣት ባርያ ነው።


በዚ​ያም ቀን ኢያሱ እነ​ር​ሱን ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችና ውኃ ቀጂ​ዎች አደ​ረ​ጋ​ቸው። ስለ​ዚ​ህም የገ​ባ​ዖን ሰዎች ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ረ​ጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ጨት ቈራ​ጮች፥ ውኃም ቀጂ​ዎች ሆኑ።


በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል ‘እናንተ ርጉማን! ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።


የሆ​ድህ ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህም ፍሬ፥ የላ​ም​ህም መንጋ፥ የበ​ግ​ህም መንጋ ርጉ​ማን ይሆ​ናሉ።


ቍጣ​ቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበ​ርና፤ ኵር​ፍ​ታ​ቸ​ውም ብርቱ ነበ​ርና፤ በያ​ዕ​ቆብ እከ​ፋ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እበ​ታ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።


የከ​ነ​ዓን አባት ካምም የአ​ባ​ቱን ዕራ​ቁ​ት​ነት አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁ​ለቱ ወን​ድ​ሞቹ ነገ​ራ​ቸው።


አሁ​ንም የወ​ን​ድ​ም​ህን ደም ከእ​ጅህ ለመ​ቀ​በል አፍ​ዋን በከ​ፈ​ተች በም​ድር ላይ አንተ የተ​ረ​ገ​ምህ ነህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም እባ​ቡን አለው፥ “ይህን ስላ​ደ​ረ​ግህ ከእ​ን​ስ​ሳት ሁሉ፥ ከም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ ተለ​ይ​ተህ አንተ የተ​ረ​ገ​ምህ ሁን ፤ በደ​ረ​ት​ህና በሆ​ድ​ህም ትሄ​ዳ​ለህ፤ በሕ​ይ​ወ​ት​ህም ዘመን ሁሉ አፈ​ርን ትበ​ላ​ለህ።


ከመ​ር​ከብ የወ​ጡት የኖኅ ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከ​ነ​ዓን አባት ነው።


ኖኅም ከወ​ይኑ ስካር በነቃ ጊዜ፥ ታናሹ ልጁ ያደ​ረ​ገ​በ​ትን ዐወቀ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios