ዘሌዋውያን 26:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 በእናንተ ላይ ክፉዎች የምድርን አራዊት እሰድዳለሁ፤ ይበሉአችኋል፤ እንስሶቻችሁንም ያጠፋሉ፤ እናንተንም ያሳንሳሉ፤ መንገዶቻችሁም በረሃ ይሆናሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 የዱር አራዊትን እሰድድባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁን ይነጥቋችኋል፤ ከብቶቻችሁን ያጠፉባችኋል፤ ቍጥራችሁ ይመነምናል፤ መንገዶቻችሁም ሰው አልባ ይሆናሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 በመካከላችሁም የዱር አራዊትን እለቅባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይነጥቁአችኋል፥ እንሰሶቻችሁንም ያጠፉባችኋል፥ እናንተንም ቁጥራችሁን ያመነምኑታል፤ መንገዶቻችሁም የተራቈቱ ይሆናሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 በመካከላችሁ አደገኞች አራዊትን እልካለሁ፤ እነርሱም ልጆቻችሁን ይገድላሉ፤ ከብቶቻችሁንም ያወድማሉ፤ ከእናንተ ጥቂት ሰዎች ብቻ ስለሚቀሩ ጐዳናዎቻችሁ ሁሉ ሰው አልባ ይሆናሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 በመካከላችሁም የምድርን አራዊት እሰድዳለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይነጥቃሉ፥ እንሰሶቻችሁንም ያጠፋሉ፥ እናንተንም ያሳንሳሉ፤ መንገዶቻችሁም በረሃ ይሆናሉ። Ver Capítulo |