2 ነገሥት 15:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዖዝያንም ልጅ በኢዮአታም በሃያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮሜልዮ ልጅ በፋቁሔ ላይ ዐመፀበት፤ መትቶም ገደለው፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮሜልዩ ልጅ በፋቁሔ ላይ አሤረበት፤ አደጋ ጥሎም ገደለው፤ የዖዝያን ልጅ ኢዮአታም በነገሠ በሃያኛው ዓመትም ሆሴዕ በፋቁሔ እግር ተተክቶ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዖዝያ ልጅ ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠ በሀያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በንጉሥ ፋቁሔ ላይ ሤራ ጠነሰሰ፤ እርሱንም ገድሎ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዖዝያ ልጅ ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠ በሃያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በንጉሥ ፋቁሔ ላይ ሤራ ጠነሰሰ፤ እርሱንም ገድሎ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዖዝያንም ልጅ በኢዮአታም በሀያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮሜልዩ ልጅ በፋቁሔ ላይ ተማማለ፤ መትቶም ገደለው፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ። |
የሠራዊቱም አለቃ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ከዳው፤ በሰማርያም በንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአርጎብና ከአርያ ጋር መታው፤ ከእርሱም ጋር ከገለዓዳውያን አምሳ ሰዎች ነበሩ፤ ገደለውም፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።
በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
“እኒህ ሕዝብ በቀስታ በሚሄደው በሰሊሆም ውኃ ቍርጥ ምክርን መከሩ፤ ረአሶንንና የሮሜልዩን ልጅ ያነግሡላቸው ዘንድ ይወዳሉና።
የእስራኤል ቤት ሆይ! ከኀጢአታችሁ ክፋት የተነሣ እንዲሁ አደርግባችኋለሁ፤ በነጋም ጊዜ የእስራኤልን ንጉሥ ይጥሉታል።