Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 15:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከዚያም የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮሜልዩ ልጅ በፋቁሔ ላይ አሤረበት፤ አደጋ ጥሎም ገደለው፤ የዖዝያን ልጅ ኢዮአታም በነገሠ በሃያኛው ዓመትም ሆሴዕ በፋቁሔ እግር ተተክቶ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 የዖዝያ ልጅ ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠ በሀያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በንጉሥ ፋቁሔ ላይ ሤራ ጠነሰሰ፤ እርሱንም ገድሎ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 የዖዝያ ልጅ ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠ በሃያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በንጉሥ ፋቁሔ ላይ ሤራ ጠነሰሰ፤ እርሱንም ገድሎ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 በዖ​ዝ​ያ​ንም ልጅ በኢ​ዮ​አ​ታም በሃ​ያ​ኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮ​ሜ​ልዮ ልጅ በፋ​ቁሔ ላይ ዐመ​ፀ​በት፤ መት​ቶም ገደ​ለው፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 በዖዝያንም ልጅ በኢዮአታም በሀያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮሜልዩ ልጅ በፋቁሔ ላይ ተማማለ፤ መትቶም ገደለው፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 15:30
15 Referencias Cruzadas  

የይሁዳ ንጉሥ አካዝ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፣ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሰማርያ ከተማ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ዘጠኝ ዓመትም ገዛ።


ስለዚህ ቤቴል ሆይ፤ ክፋትሽ ታላቅ ስለ ሆነ፣ በአንቺም ላይ እንደዚሁ ይሆናል፤ ያ ቀን ሲደርስም፣ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።”


ሰማርያና ንጉሧ፣ በውሃ ላይ እንዳለ ኵበት ተንሳፍፈው ይጠፋሉ።


እነርሱም፣ “እኛ ንጉሥ የለንም፤ እግዚአብሔርን አላከበርንምና፤ ንጉሥ ቢኖረንስ፣ ምን ሊያደርግልን ይችል ነበር?” ይላሉ።


“ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈስሰውን የሰሊሆምን ውሆች ትቶ፣ በረአሶንና በሮሜልዩ ልጅ ተደስቷልና።


በዚያ ጊዜ ንጉሡ አካዝ ወደ አሦር ንጉሥ ልኮ ርዳታ ጠየቀ፤


የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት፣ የይሁዳ ንጉሥ፣ የኢዮአታም ልጅ አካዝ ነገሠ።


ከጦር አለቆቹ አንዱ የሆነው የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ አሤረበት፤ ዐምሳ የገለዓድ ሰዎች ይዞ በመሄድ፣ ሰማርያ ቤተ መንግሥት ባለው ምሽግ ፋቂስያስን ከአርጎብና ከአርያ ጋራ ገደለው፤ በእግሩም ተተክቶ ነገሠ።


የኢያቤስ ልጅ ሰሎም በዘካርያስ ላይ አሤረበት፤ በሕዝቡ ፊት አደጋ ጥሎ ገደለው፤ በእግሩም ተተክቶ ነገሠ።


በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን፣ የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ ዒዮን፣ አቤልቤትመዓካን፣ ያኖዋን፣ ቃዴስንና አሦርን፣ ገለዓድንና ገሊላን፣ የንፍታሌምንም ምድር ጭምር ያዘ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ወደ አሦር ወሰደው።


በፋቁሔ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ የፈጸማቸውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?


ነገር ግን ሕፃኑ ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ከመቻሉ በፊት የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት ምድር ባድማ ይሆናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios