Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሆሴዕ 10:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ክፋት የተ​ነሣ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ጋም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ይጥ​ሉ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህ ቤቴል ሆይ፤ ክፋትሽ ታላቅ ስለ ሆነ፣ በአንቺም ላይ እንደዚሁ ይሆናል፤ ያ ቀን ሲደርስም፣ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ቤቴል ሆይ! ከኃጢአታችሁም ክፋት የተነሣ እንዲሁ ይደረግባችኋል፤ ጎሕ ሲቀድ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የቤትኤል ከተማ ነዋሪዎች ሆይ! በሠራችሁት ከባድ ኃጢአት ምክንያት በእናንተም ላይ ይህንኑ የመሰለ ጥፋት ይደርስባችኋል፤ ጦርነቱም እንደ ተነሣ ጎሕ ሲቀድ የእስራኤል ንጉሥ ወዲያውኑ ይገደላል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከኃጢአታችሁም ክፋት የተነሣ ቤቴል እንዲሁ ያደርግባችኋል፥ በነጋ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 10:15
8 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም እን​ዲህ እላ​ለሁ፤ በሦ​ስት ዓመት ውስጥ እንደ ምን​ደኛ ዓመት የሞ​ዓብ ክብር ከብዙ ሀብ​ትዋ ጋር ይዋ​ረ​ዳል፤ በቍ​ጥ​ርም ጥቂት ይቀ​ራል፤ ክብ​ር​ዋም አይ​ገ​ኝም።


በሕ​ዝ​ብ​ህም መካ​ከል ጥፋት ይነ​ሣል፤ እና​ትም በል​ጆ​ችዋ ላይ በተ​ጣ​ለች ጊዜ የሰ​ል​ማን አለቃ ቤት​አ​ር​ብ​ኤ​ልን በጦ​ር​ነት ቀን እን​ዳ​ፈ​ረሰ፥ አም​ባ​ዎ​ችህ ሁሉ ይፈ​ር​ሳሉ።


አሁ​ንም፥ “ንጉሥ የለ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ራ​ን​ምና፤ ንጉ​ሥስ ምን ያደ​ር​ግ​ል​ናል?” ይላሉ።


የሰ​ማ​ርያ ሰዎች በቤ​ት​አ​ዌን እን​ቦሳ አጠ​ገብ ይኖ​ራሉ፤ ሕዝቡ ያለ​ቅ​ሱ​ለ​ታል፤ ክብ​ሩም ከእ​ርሱ ዘንድ ወጥ​ቶ​አ​ልና እን​ዳ​ዘ​ኑ​በት እን​ዲሁ በክ​ብሩ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


ሰማ​ርያ ንጉ​ሥ​ዋን እንደ ጥራጊ በውኃ ላይ ጣለ​ችው።


እስ​ራ​ኤል ሕፃን በነ​በረ ጊዜ ወደ​ድ​ሁት፤ ልጄ​ንም ከግ​ብፅ ጠራ​ሁት፤


እን​ግ​ዲህ ያ መል​ካም ነው ብዬ የማ​ስ​በው ነገር በውኑ አጥፊ ሆነኝ እላ​ለ​ሁን? አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ኀጢ​አት ኀጢ​አት እንደ ሆነች በታ​ወ​ቀች ጊዜ ሞትን አበ​ዛ​ች​ብኝ፤ ከዚ​ያም ትእ​ዛዝ የተ​ነሣ ኀጢ​አ​ተ​ናው እን​ዲ​ታ​ወቅ፥ ኀጢ​አ​ትም ተለ​ይታ እን​ድ​ት​ታ​ወቅ ኦሪት መል​ካ​ሙን ከክፉ ልት​ለይ ተሠ​ር​ታ​ለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos