Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 15:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የኢ​ያ​ቢ​ስም ልጅ ሴሎም፤ ሌሎ​ችም ከዱት፤ በይ​ብ​ል​ዓም መት​ተው ገደ​ሉት፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ሴሎም ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የኢያቤስ ልጅ ሰሎም በዘካርያስ ላይ አሤረበት፤ በሕዝቡ ፊት አደጋ ጥሎ ገደለው፤ በእግሩም ተተክቶ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሻሉም ተብሎ የሚጠራው የያቤሽ ልጅ ሤራ በማድረግ ዪብለዓም ተብላ በምትጠራው ስፍራ ንጉሥ ዘካርያስን ገድሎ በእርሱ እግር ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሻሉም ተብሎ የሚጠራው የያቤሽ ልጅ ሤራ በማድረግ ዪብለዓም ተብላ በምትጠራው ስፍራ ንጉሥ ዘካርያስን ገድሎ በእርሱ እግር ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የኢያቤስም ልጅ ሰሎም ተማማለበት፤ በይብልዓም መትቶ ገደለው፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 15:10
16 Referencias Cruzadas  

በይ​ሁዳ ንጉሥ በአሳ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ባኦስ ናባ​ጥን ገደ​ለው፥ በፋ​ን​ታ​ውም ነገሠ።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም የኢ​ያ​ሙ​ሃት ልጅ ኢያ​ዜ​ክ​ርና የሳ​ሜር ልጅ ኢያ​ዛ​ብድ መቱት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት፤ ልጁም አሜ​ስ​ያስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የዐ​መፅ መሐላ አደ​ረ​ጉ​በት፤ እር​ሱም ወደ ለኪሶ ኮበ​ለለ፤ ወደ ለኪ​ሶም ተከ​ተ​ሉት፤ በዚ​ያም ገደ​ሉት።


የቀ​ረ​ውም የዘ​ካ​ር​ያስ ነገር፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የጋ​ዲም ልጅ ምና​ሔም ከቴ​ር​ሳ​ላቅ ወጥቶ ወደ ሰማ​ርያ ሄደ፤ በሰ​ማ​ር​ያም የኢ​ያ​ቢ​ስን ልጅ ሴሎ​ምን መታ፤ ገደ​ለ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።


ምና​ሔ​ምም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፤ ልጁም ፋቂ​ስ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ከዳው፤ በሰ​ማ​ር​ያም በን​ጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአ​ር​ጎ​ብና ከአ​ርያ ጋር መታው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ው​ያን አምሳ ሰዎች ነበሩ፤ ገደ​ለ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።


በዖ​ዝ​ያ​ንም ልጅ በኢ​ዮ​አ​ታም በሃ​ያ​ኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮ​ሜ​ልዮ ልጅ በፋ​ቁሔ ላይ ዐመ​ፀ​በት፤ መት​ቶም ገደ​ለው፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።


አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ካሳ​ታ​ቸው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት አል​ራ​ቀም።


ኢዩም በእጁ ቀስ​ቱን ለጠጠ፤ ኢዮ​ራ​ም​ንም በጫ​ን​ቃው መካ​ከል ወጋው ፤ ፍላ​ጻ​ውም በልቡ አለፈ፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ውስጥ በጕ​ል​በቱ ላይ ወደቀ።


ኢዩም ወደ ከተማ በገባ ጊዜ፥ “ጌታ​ውን የገ​ደለ ዘምሪ ሰላም ነውን?” አለ​ችው።


ሁሉም እንደ ምድጃ ግለ​ዋል፤ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ወደቁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል የሚ​ጠ​ራኝ የለም።


ራሳ​ቸ​ውን አነ​ገሡ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አይ​ደ​ለም፤ አለ​ቆ​ች​ንም አደ​ረጉ፤ እኔም አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ ለጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ከብ​ራ​ቸ​ውና ከወ​ር​ቃ​ቸው ጣዖ​ታ​ትን ለራ​ሳ​ቸው አደ​ረጉ።


መሳ​ቂያ የሆኑ የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ይፈ​ር​ሳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መቅ​ደ​ሶች ባድማ ይሆ​ናሉ፤ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ቤት ላይ በሰ​ይፍ እነ​ሣ​ለሁ” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos