1 ሳሙኤል 25:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሞተ፤ እስራኤልም ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፤ በአርማቴምም በቤቱ ቀበሩት። ዳዊትም ተነሥቶ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም ሞተ፤ እስራኤል ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፤ አርማቴም ባለው ቤቱም ቀበሩት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም ሞተ፤ መላው እስራኤል ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፤ ራማ ባለው ቤቱም ቀበሩት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤል ሞተ፤ መላው እስራኤላውያንም በአንድነት መጥተው አለቀሱለት፤ ከዚያም በኋላ በራማ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ቀበሩት። ከዚያም በኋላ ዳዊት ወደ ፋራን ምድረ በዳ ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ሞተ፥ እስራኤልም ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፥ በአርማቴምም በቤቱ ቀበሩት። ዳዊትም ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ። |
ሣራም በቈላ ውስጥ ባለች አርባቅ በምትባል ከተማ ሞተች፤ እርስዋም በከነዓን ምድር ያለች ኬብሮን ናት፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያዝንላትና ሊያለቅስላት ተነሣ።
በዚያች ምድር የሚኖሩ የከነዓን ሰዎችም በአጣድ አውድማ የሆነውን ልቅሶ በአዩ ጊዜ፥ “የግብፅ ልቅሶ እንዲህ ታላቅ ነውን?” አሉ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም “ላሐ ግብፅ” ብለው ጠሩት፤ እርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ነው።
ቍጥሩ ከባሕር አሸዋ የሚበልጥ በደልን በድያለሁና፥ ኀጢአቴም ብዙ ነውና፤ ከበደሌም ብዛት የተነሣ ቀና ብዬ የሰማይን ርዝመት አይ ዘንድ አገባቤ አይደለም። ሰውነቴን ከኀጢአቴ አሳርፋት ዘንድ በብረት ቀፎ ደከምሁ፤ በዚህም ደግሞ አላረፍሁም፤ መዓትህን አነሣሥቻለሁና፥
ገሥግሠውም በቃዴስ ፋራን ምድረ በዳ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ደረሱ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።
የእስራኤልም ልጆች በዮርዳኖስ በኢያሪኮ አቅራቢያ በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለቀሱለት፤ ለሙሴም ያለቀሱለት የልቅሶው ወራት ተፈጸመ።
ማልደውም ተነሥተው ለእግዚአብሔር ሰግደው ሄዱ፤ ወደ ቤታቸውም ወደ አርማቴም ደረሱ፤ ሕልቃናም ሚስቱን ሐናን ዐወቃት፤ እግዚአብሔርም አሰባት፤ ፀነሰችም።
ሳሙኤል ግን ሞቶ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ አልቅሰውለት ነበር፤ በከተማውም በአርማቴም ቀብረውት ነበር። ሳኦልም መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር አጥፍቶ ነበር።
ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፤ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።