Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 34:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዮ​ር​ዳ​ኖስ በኢ​ያ​ሪኮ አቅ​ራ​ቢያ በሞ​ዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለሙ​ሴም ያለ​ቀ​ሱ​ለት የል​ቅ​ሶው ወራት ተፈ​ጸመ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የልቅሶውና የሐዘኑ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ፣ እስራኤላውያን ለሙሴ በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን አለቀሱለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የእስራኤልም ሕዝብ የሐዘኑ ጊዜ እስከሚያበቃ ድረስ ለሙሴ በማዘንሠላሳ ቀን በሞዓብ ሜዳ አለቀሱለት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የእስራኤልም ሕዝብ የሐዘኑ ጊዜ እስከሚያበቃ ድረስ ለሙሴ በማዘን ሠላሳ ቀን በሞአብ ሜዳ አለቀሱለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የእስራኤልም ልጆች በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለቀሱለት፤ ለሙሴም ያለቀሱለት የልቅሶው ወራት ተፈጸመ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 34:8
9 Referencias Cruzadas  

በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወዳ​ለ​ችው ወደ አጣድ አው​ድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅ​ሶም አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለአ​ባ​ቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደ​ረ​ገ​ለት።


አርባ ቀንም ፈጸ​ሙ​ለት፤ ሽቱ የሚ​ቀ​ቡ​በ​ትን ቀን እን​ዲሁ ይቈ​ጥ​ራ​ሉና፤ የግ​ብ​ፅም ሰዎች ሰባ ቀን አለ​ቀ​ሱ​ለት።


የኦ​ር​ዮም ሚስት ባልዋ ኦርዮ እንደ ሞተ በሰ​ማች ጊዜ ለባ​ልዋ አለ​ቀ​ሰች።


ጻድቅ ሰው እን​ደ​ጠፋ አያ​ችሁ፤ ይህ​ንም በል​ባ​ችሁ አላ​ሰ​ባ​ች​ሁም፤ ጻድ​ቃን ሰዎች ይወ​ገ​ዳሉ፤ ጻድ​ቅም ከክ​ፋት ፊት እንደ ተወ​ገደ ማንም አያ​ስ​ተ​ው​ልም።


ማኅ​በ​ሩም ሁሉ አሮን እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ለአ​ሮን ሠላሳ ቀን አለ​ቀሱ።


እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስ​ንም ደጋግ ሰዎች አን​ሥ​ተው ቀበ​ሩት፤ ታላቅ ልቅ​ሶም አለ​ቀ​ሱ​ለት።


ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜዉ መቶ ሃያ ዓመት ነበረ፤ ዐይ​ኖ​ቹም አል​ፈ​ዘ​ዙም፤ ጕል​በ​ቱም አል​ደ​ከ​መም ነበር።


ሙሴም እጆ​ቹን ስለ ጫነ​በት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥ​በ​ብን መን​ፈስ ተሞላ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ታዘ​ዙ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።


ሳሙ​ኤ​ልም ሞተ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ በአ​ር​ማ​ቴ​ምም በቤቱ ቀበ​ሩት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ወረደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos