የጌራራ እረኞች ከይስሐቅ እረኞች ጋር፥ “ውኃው የእኛ ነው” ሲሉ ተጣሉ፤ የዚያችንም ጕድጓድ ስም “ዐዘቅተ ዐመፃ” ብሎ ጠራት፤ እነርሱ በድለውታልና።
1 ሳሙኤል 21:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ከሳኦል አገልጋዮች አንድ ሰው በኔሴራ አቅራቢያ በዚያ በእግዚአብሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶርያዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳኦልም በቅሎዎች ጠባቂ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያችም ዕለት ከሳኦል አገልጋዮች አንዱና የእረኞቹ አለቃ የሆነው ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያው በእግዚአብሔር ፊት እንዲቈይ ተገዶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያችም ዕለት ከሳኦል አገልጋዮች አንዱና የእረኞቹ አለቃ የሆነው ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያው በጌታ ፊት እንዲቆይ ተገዶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳኦል እረኞች አለቃ የሆነው ኤዶማዊው ዶይቅ በዚያኑ ቀን ሃይማኖታዊ ሥርዓትን ለመፈጸም በዚያ ተገኝቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ከሳኦል ባሪያዎች አንድ ሰው በዚያ በእግዚአብሔር ፊት ተገኝቶ ነበር፥ ስሙም ኤዶማዊው ዶይቅ ነበረ፥ ለሳኦልም የእረኞቹ አለቃ ነበረ። |
የጌራራ እረኞች ከይስሐቅ እረኞች ጋር፥ “ውኃው የእኛ ነው” ሲሉ ተጣሉ፤ የዚያችንም ጕድጓድ ስም “ዐዘቅተ ዐመፃ” ብሎ ጠራት፤ እነርሱ በድለውታልና።
በሳሮንም በሚሰማሩ ከብቶች ላይ ሳሮናዊው ሰጥራይ ሹም ነበረ፤ በሸለቆዎቹም ውስጥ በነበሩት ከብቶች ላይ የዓድላይ ልጅ ሳፋጥ ሹም ነበረ፤
በምድረ በዳውም ግንቦችን ሠራ፤ ብዙ ጕድጓድም ማሰ፤ በቆላውና በደጋው ብዙ እንስሶች ነበሩትና፤ ደግሞም እርሻ ይወድድ ነበርና በተራራማውና በፍሬያማው ስፍራ አራሾችና የወይን አትክልተኞች ነበሩት።
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፤ ቃልህንም ይሰማሉ፤ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባቸውም ጣዖታትን ይከተላልና።
የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነቷ እንደ ነበረች ወደ አባቷ ቤት ብትመለስ፥ ከአባቷ እንጀራ ትብላ፤ ከሌላ ወገን የሆነ ባዕድ ሰው ግን ከእርሱ አይብላ።
“የስንዴ ዱቄት ወስደህ ዐሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር፤ በእያንዳንዱ ኅብስት ውስጥ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ ይሁን።
“እህልን እንሸጥ ዘንድ መባቻው መቼ ያልፋል? የኢፍ መስፈሪያውንም እያሳነስን፥ ሰቅሉንም እያበዛን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እያታለልን፥
እነሆም፥ ሳኦል ከእርሻው አርፍዶ መጣ፤ ሳኦልም፥ “ሕዝቡ የሚያለቅስ ምን ሆኖ ነው?” አለ። የኢያቢስንም ሰዎች ነገር ነገሩት።
ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፤ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከቢዖርም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።
ዳዊትም አቤሜሌክን፥ “የንጉሥ ጉዳይ ስላስቸኰለኝ ሰይፌንና መሣሪያዬን አላመጣሁምና በአንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ እንዳለ እይልኝ” አለው።
ዳዊት አብያታርን፦ ሶርያዊው ዶይቅ በዚያ መኖሩን ባየሁ ጊዜ፥ “ለሳኦል በርግጥ ይነግራል ብዬ በዚያ ቀን አውቄዋለሁ፤ ለአባትህ ቤት ነፍስ ሁሉ ጥፋት በደለኛው እኔ ነኝ።
የሳኦልም በቅሎዎች ጠባቂ ሶርያዊው ዶይቅ መልሶ፥ “የእሴይ ልጅ ወደ ኖብ ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ ካህኑ አቤሜሌክ ሲመጣ አይቼዋለሁ።