Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 22:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የካ​ህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብት​ፋታ፥ ልጅም ባይ​ኖ​ራት፥ በብ​ላ​ቴ​ን​ነቷ እንደ ነበ​ረች ወደ አባቷ ቤት ብት​መ​ለስ፥ ከአ​ባቷ እን​ጀራ ትብላ፤ ከሌላ ወገን የሆነ ባዕድ ሰው ግን ከእ​ርሱ አይ​ብላ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ይሁን እንጂ የካህኑ ልጅ ባሏ ቢሞት ወይም ብትፋታ፣ ልጆችም ባይኖሯትና እንደ ልጅነት ጊዜዋ በአባቷ ቤት ለመኖር ብትመለስ፣ ከአባቷ ድርሻ መብላት ትችላለች፤ ያልተፈቀደለት ሰው ግን ከተቀደሰው መሥዋዕት መብላት አይችልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነትዋ እንደ ነበረች ወደ አባትዋ ቤት ብትመለስ፥ ከአባትዋ እንጀራ ትብላ፤ ማናቸውም ምእመን ግን ከእርሱ አይብላ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ነገር ግን ልጅ ሳትወልድ ባልዋ የሞተባት ወይም ከባልዋ በመፋታት ወደ አባቷ ቤት ተመልሳ መጥታ በጥገኝነት የምትኖር የካህኑ ልጅ በልጅነትዋ ታደርገው እንደ ነበረው ሁሉ የአባቷ ድርሻ ከሆነው ቅዱስ ነገር ትብላ፤ ሆኖም ከካህኑ ቤተሰብ ሌላ ሰው የተቀደሰውን ነገር መብላት የለበትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነትዋ እንደ ነበረች ወደ አባትዋ ቤት ብትመለስ፥ ከአባትዋ እንጀራ ትብላ፤ ልዩ ሰው ግን ከእርሱ አይብላ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 22:13
11 Referencias Cruzadas  

ይሁ​ዳም ምራ​ቱን ትዕ​ማ​ርን፥ “ልጄ ሴሎም እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በአ​ባ​ትሽ ቤት መበ​ለት ሆነሽ ተቀ​መጪ” አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወን​ድ​ሞቹ እን​ዳ​ይ​ሞ​ት​ብኝ ብሎ​አ​ልና። ትዕ​ማ​ርም ሄዳ በአ​ባቷ ቤት ተቀ​መ​ጠች።


ሐቲ​ር​ሰ​ስ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳኑ አት​በ​ሉም” አላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን አላ​ቸው፥ “ይህ የፋ​ሲካ ሕግ ነው፤ ከእ​ርሱ ባዕድ ሰው አይ​ብላ።


ለመ​ክ​በ​ራ​ቸው እጆ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ድሱ ዘንድ በተ​ቀ​ደ​ሱ​በት በዚያ ቦታ ይብ​ሉት፤ የባ​ዕድ ልጅ ግን አይ​ብ​ላው፤ የተ​ቀ​ደሰ ነውና።


የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁም፤ ነገር ግን የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የሚ​ጠ​ብቁ ሌሎ​ችን ለራ​ሳ​ችሁ ሾማ​ችሁ።”


እነ​ዚ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ለአ​ን​ተና ለል​ጆ​ችህ ሥር​ዐት እን​ዲ​ሆኑ ስለ ተሰጡ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ፍር​ም​ባና ወርች አንተ፥ ከአ​ንተ ጋርም ልጆ​ችህ፥ ቤተ​ሰ​ብ​ህም ተለ​ይቶ በን​ጹሕ ስፍራ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


“ከባ​ዕድ ወገን የሆነ ሰው ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ፤ የካ​ህ​ኑም እን​ግዳ፥ ደመ​ወ​ዘ​ኛ​ውም ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ።


የካ​ህ​ንም ልጅ ከሌላ ወገን ጋር ብት​ጋባ፥ እር​ስዋ ከተ​ቀ​ደ​ሰው ዐሥ​ራት አት​ብላ።


ከቤ​ቱም ከወ​ጣች በኋላ ሌላ ወንድ ብታ​ገባ፥


በዚ​ያም ቀን ከሳ​ኦል አገ​ል​ጋ​ዮች አንድ ሰው በኔ​ሴራ አቅ​ራ​ቢያ በዚያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳ​ኦ​ልም በቅ​ሎ​ዎች ጠባቂ ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos