Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 22:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “ከባ​ዕድ ወገን የሆነ ሰው ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ፤ የካ​ህ​ኑም እን​ግዳ፥ ደመ​ወ​ዘ​ኛ​ውም ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ ‘ከካህን ቤተ ሰብ በቀር የካህኑ እንግዳም ሆነ ቅጥር ሠራተኛ የተቀደሰውን መሥዋዕት አይብላ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 “ማናቸውም ምእመን ከተቀደሰው አይብላ የካህኑም እንግዳ የሆነ እና ተቀጥሮ የሚያገለግል ከተቀደሰው አይብላ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “ከተቀደሰው ስጦታ መብላት የሚችለው የካህን ቤተሰብ የሆነ ሰው ብቻ ነው፤ ሌላ ሰው ግን ከእርሱ አይብላ፤ ከካህኑ ጋር በእንግድነት ወይም ተቀጥሮ የሚኖር አይብላ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ልዩ ሰው ከተቀደሰው አይብላ የካህኑም እንግዳ ደመወዘኛውም ከተቀደሰው አይብላ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 22:10
11 Referencias Cruzadas  

ካህኑ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በእ​ርሱ ፋንታ ትኩስ እን​ጀራ ይደ​ረግ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከአ​ለው ኅብ​ስት በቀር ሌላ እን​ጀራ አል​ነ​በ​ረ​ምና የቍ​ር​ባ​ኑን ኅብ​ስት ሰጠው።


ለመ​ክ​በ​ራ​ቸው እጆ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ድሱ ዘንድ በተ​ቀ​ደ​ሱ​በት በዚያ ቦታ ይብ​ሉት፤ የባ​ዕድ ልጅ ግን አይ​ብ​ላው፤ የተ​ቀ​ደሰ ነውና።


ጥገ​ኛና ሞያ​ተኛ ግን ከእ​ርሱ አይ​ብሉ።


የካ​ህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብት​ፋታ፥ ልጅም ባይ​ኖ​ራት፥ በብ​ላ​ቴ​ን​ነቷ እንደ ነበ​ረች ወደ አባቷ ቤት ብት​መ​ለስ፥ ከአ​ባቷ እን​ጀራ ትብላ፤ ከሌላ ወገን የሆነ ባዕድ ሰው ግን ከእ​ርሱ አይ​ብላ።


አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት አቁ​ማ​ቸው፤ ክህ​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በመ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ ያለ​ው​ንም ሁሉ ይጠ​ብቁ፤ ከሌላ ወገን የዳ​ሰሰ ቢኖር ይገ​ደል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን አላ​ቸው፥ “ይህ የፋ​ሲካ ሕግ ነው፤ ከእ​ርሱ ባዕድ ሰው አይ​ብላ።


የቅ​ዱ​ሱ​ንና የቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳ​ኑን የአ​ም​ላ​ኩን መባ ይብላ፤


በዚ​ያም ቀን ከሳ​ኦል አገ​ል​ጋ​ዮች አንድ ሰው በኔ​ሴራ አቅ​ራ​ቢያ በዚያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳ​ኦ​ልም በቅ​ሎ​ዎች ጠባቂ ነበረ።


ሐቲ​ር​ሰ​ስ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳኑ አት​በ​ሉም” አላ​ቸው።


የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁም፤ ነገር ግን የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የሚ​ጠ​ብቁ ሌሎ​ችን ለራ​ሳ​ችሁ ሾማ​ችሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios