ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፤ ይህም ከአባቴ የወለድሁት ማለት ነው። እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው።
1 ሳሙኤል 14:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፤ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከቢዖርም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል በእስራኤል ላይ በትረ መንግሥቱን ከጨበጠ በኋላ፣ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ማለትም ሞዓብን፣ አሞናውያንን፣ ኤዶምን፣ የሱባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በሄደበት ሁሉ ድል ይነሣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል በእስራኤል ላይ ከነገሠ በኋላ፥ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ሞዓብን፥ አሞናውያንን፥ ኤዶምን፥ የጾባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል በእስራኤል ከነገሠ በኋላ፥ በሁሉም ስፍራ የሚገኙ ጠላቶቹን ወጋ፤ እነርሱም የሞአብ፥ የዐሞንና የኤዶም ሕዝቦች፥ የጾባ ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያን ናቸው፤ በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ሆነ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፥ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ይዋጋ ነበር፥ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር። |
ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፤ ይህም ከአባቴ የወለድሁት ማለት ነው። እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው።
ታናሺቱም ደግሞ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም የወገኔ ልጅ ስትል አሞን ብላ ጠራችው፤ እርሱም እስከ ዛሬ የአሞናውያን አባት ነው።
ከሞቱት ደምና ከኀያላን ስብ፥ የዮናታን ቀስት ባዶዋን አልተመለሰችም፤ የሳኦልም ሰይፍ ባዶዋን አልተመለሰችም።
የአሞንም ልጆች የዳዊት ወገኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከቤትሮዖብ ሶርያውያንና ከሱባ ሶርያውያን ሃያ ሺህ እግረኞችን፥ ከአማሌቅ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎችን፥ ከአስጦብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ።
እግዚአብሔርም ደግሞ ከጌታው ከሱባ ንጉሥ ከአድርአዛር የኰበለለውን የኤልያዳን ልጅ ሬዞንን ጠላት አድርጎ አስነሣበት።
እግዚአብሔርም የእስራኤልን ዘር ከሰማይ በታች ይደመስስ ዘንድ አልተናገረም፤ ነገር ግን በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም እጅ አዳናቸው።
አሁንም እነሆ፥ ንጉሡ በፊታችሁ ይሄዳል፤ እኔም አርጅቻለሁ፤ እንግዲህም አርፋለሁ፤ እነሆም፥ ልጆቼ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ እኔም ከሕፃንነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊታችሁ ሄድሁ።
በሳኦልም ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፤ ሳኦልም ጽኑ ወይም ኀያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰበስብ ነበር።
በዚያም ቀን ከሳኦል አገልጋዮች አንድ ሰው በኔሴራ አቅራቢያ በዚያ በእግዚአብሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶርያዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳኦልም በቅሎዎች ጠባቂ ነበረ።