Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 36:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዔሳ​ውም በሴ​ይር ተራራ ተቀ​መጠ፤ ዔሳ​ውም ኤዶም ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ፥ ዔሳው ኤዶም ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው በተራራማው አገር በኤዶም ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ ዔሳውም ኤዶም ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 36:8
21 Referencias Cruzadas  

በሴ​ይር ተራ​ራ​ዎች ያሉ የኬ​ሬ​ዎስ ሰዎ​ች​ንም በበ​ረሃ አጠ​ገብ እስከ አለ​ችው እስከ ፋራን ዛፍ ድረስ መቱ​አ​ቸው።


ዔሳ​ውም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ከም​ስር ንፍ​ሮህ አብ​ላኝ፤ እኔ እጅግ ደክ​ሜ​አ​ለ​ሁና” አለው፤ ስለ​ዚ​ህም ስሙ ኤዶም ተባለ።


ያዕ​ቆ​ብም ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም ሀገር በፊቱ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤


እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው፦ ባሪ​ያህ ያዕ​ቆብ እን​ዲህ አለ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ በላባ ዘንድ በስ​ደት ተቀ​መ​ጥሁ፤ እስከ ዛሬ ድረስ ቈየሁ፤


ኤዶም የተ​ባ​ለው የዔ​ሳው ትው​ልድ እን​ዲህ ነው።


መግ​ዴ​ኤል መስ​ፍን፥ ኤራም መስ​ፍን፤ እነ​ዚህ በግ​ዛ​ታ​ቸው ምድር በየ​መ​ኖ​ሪ​ያ​ቸው የኤ​ዶም መሳ​ፍ​ንት ናቸው። የኤ​ዶ​ማ​ው​ያ​ንም አባት ይህ ዔሳው ነው።


በሴ​ይር ተራራ የሚ​ኖሩ የኤ​ዶ​ማ​ው​ያን አባት የዔ​ሳው ትው​ል​ድም እን​ዲህ ነው።


ከስ​ም​ዖ​ንም ልጆች አም​ስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም የይ​ሰዔ ልጆች ፥ ፈላ​ጥያ፥ ነዓ​ርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝ​ኤል ነበሩ።


አሁ​ንም እነሆ፥ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብዕ ምድር በወጡ ጊዜ ያል​ፉ​ባ​ቸው ዘንድ ያል​ፈ​ቀ​ድ​ህ​ላ​ቸው የአ​ሞ​ንና የሞ​ዓብ ልጆች፥ የሴ​ይ​ርም ተራራ ሰዎች እን​ዳ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ፈቀቅ ብለው ነበር።


የአ​ሞ​ንና የሞ​ዓብ ልጆ​ችም በሴ​ይር ተራራ በሚ​ኖ​ሩት ላይ ፈጽ​መው ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸው ዘንድ፥ ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ተነ​ሥ​ተ​ው​ባ​ቸው ነበር፤ በሴ​ይ​ርም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ካጠፉ በኋላ እርስ በር​ሳ​ቸው ሊጠ​ፋፉ ተነሡ።


በሞ​ዓ​ብና በአ​ሞ​ንም ልጆች መካ​ከል፥ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ የነ​በሩ አይ​ሁድ ሁሉ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ እን​ዳ​ስ​ቀረ፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በላ​ያ​ቸው እንደ ሾመው ሰሙ።


የአ​ብ​ድዩ ራእይ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ኤዶ​ም​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰማሁ፤ ከባ​ቢን ወደ አሕ​ዛብ ልኮ፥ “ተነሡ፤ በላ​ይ​ዋም እን​ነ​ሣና እን​ው​ጋት።


በተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀም ዓለት ውስጥ እን​ደ​ሚ​ኖር- ማደ​ሪ​ያ​ው​ንም ከፍ ከፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በል​ቡም፦ ወደ ምድር የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ማን ነው? እን​ደ​ሚል፥ የል​ብህ ትዕ​ቢት እጅግ አኵ​ር​ቶ​ሃል።


ተራሮቹንም በረሃ አደረግኋቸው፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች አሳልፌ ሰጠኋቸው።


ሖራ​ው​ያ​ንን ከፊ​ታ​ቸው አጥ​ፍቶ በሴ​ይር ለተ​ቀ​መ​ጡት ለዔ​ሳው ልጆች እን​ዳ​ደ​ረገ እነ​ርሱ ወረ​ሱ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​መጡ።


ሕዝ​ቡ​ንም እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ በሴ​ይር ላይ በተ​ቀ​መ​ጡት በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በዔ​ሳው ልጆች ሀገር ታል​ፋ​ላ​ችሁ፤ እነ​ርሱ ይፈ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ እን​ግ​ዲህ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።


የሴ​ይ​ርን ተራራ ለዔ​ሳው ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከም​ድ​ራ​ቸው የጫማ መር​ገጫ ታህል እን​ኳን አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና አት​ጣ​ሉ​አ​ቸው።


ለይ​ስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዔሳ​ውን ሰጠ​ሁት፤ ለዔ​ሳ​ውም የሴ​ይ​ርን ተራራ ርስት አድ​ርጌ ሰጠ​ሁት፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚ​ያም ታላቅ ሕዝብ ሆኑ፤ በዙም፤ በረ​ቱም፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም መከራ አጸ​ኑ​ባ​ቸው።


ሳኦ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አጸና፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉት ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞ​ዓ​ብም፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ ከቢ​ዖ​ርም፥ ከሱ​ባም ነገ​ሥ​ታት፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየ​ሄ​ደ​በ​ትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos