ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላት ሀገሮችን ይወርሳሉ፤
1 ሳሙኤል 13:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ተሰበሰቡ፤ ሠላሳ ሺህ ሰረገሎች፥ ስድስት ሺህም ፈረሰኞች፥ በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ወጥተውም ከቤቶሮን በአዜብ በኩል በማኪማስ ሰፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን ሦስት ሺሕ ሠረገሎች፣ ስድስት ሺሕ ፈረሰኞች ቍጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሰራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤትአዌን በስተምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያን ሠላሳ ሺህ ሠረገሎች፥ ስድስት ሺህ ፈረሰኞች ቁጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤትአዌን በስተ ምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያንም እስራኤላውያንን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ እነርሱም ከሠላሳ ሺህ የጦር ሠረገሎችና ከስድስት ሺህ ፈረሰኞች ጋር ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ነበራቸው፤ ሄደውም በቤትአዌን በስተምሥራቅ ሚክማስ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሸጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ተሰበሰቡ፥ ሠላሳ ሺህ ሰረገሎች ስድስትም ሺህ ፈረሰኞች በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፥ ወጥተውም ከቤትአዌን በምሥራቅ በኩል በማክማስ ሰፈሩ። |
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላት ሀገሮችን ይወርሳሉ፤
እኔ እንዲህ እመክርሃለሁ፤ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤል ሁሉ ብዛታቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆኖ ወደ አንተ ይሰብሰቡ፤ አንተም በመካከላቸው ትሄዳለህ።
አክዓብም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ ደነገጠ፤ ልብሱንም ቀደደ፤ እያለቀሰም ሄደ፤ በሰውነቱም ላይ ማቅ ለበሰ፤ ጾመም፤ ኢይዝራኤላዊው ናቡቴንም በገደለበት ቀን ደግሞ ማቅ ለብሶ ነበር።
መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተዋል፤ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፤ ጭንቀትንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።
የሰማርያ ሰዎች በቤትአዌን እንቦሳ አጠገብ ይኖራሉ፤ ሕዝቡ ያለቅሱለታል፤ ክብሩም ከእርሱ ዘንድ ወጥቶአልና እንዳዘኑበት እንዲሁ በክብሩ ደስ ይላቸዋል።
እስራኤል ሆይ! አንተ አላዋቂ አትሁን፤ አንተም ይሁዳ! ወደ ጌልጌላ አትሂድ፤ ወደ ቤትአዊንም አትውጡ፤ በሕያው እግዚአብሔርም አትማሉ።
ኢሳይያስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ስለ እስራኤል እንዲህ አለ፥ “የእስራኤል ልጆች ቍጥራቸው እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም የተረፉት ይድናሉ።
እነርሱ፥ ከእነርሱም ጋር ሠራዊቶቻቸው ሁሉ ብዛታቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆነው ወጡ፤ ፈረሶችና ሰረገሎችም እጅግ ብዙዎች ነበሩ።
በሰሜን በኩል ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ጀመረ፤ ድንበሩም ከኢያሪኮ አዜብ ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ከዚያም በተራራማው ሀገር ወደ ባሕር ወጣ፤ መውጫውም የቤቶን ምድብራይጣስ ነበረ።
ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤትአዊን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ሰዎችን ከኢያሪኮ ልኮ፥ “ውጡ፤ ጋይንም ሰልሉ” ብሎ ተናገራቸው፤ ሰዎቹም ወጡ፤ ጋይንም ሰለሉ።
ብዛታቸውም እንደ አንበጣ የሆነ ምድያማውያንና አማሌቃውያን የምሥራቅም ልጆች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት ቍጥር እንደሌለው በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነበረ።
ሳሙኤልም፥ “ያደረግኸው ምንድን ነው?” አለ። ሳኦልም፥ “ሕዝቡ ከእኔ ተለይተው እንደ ተበታተኑ፥ አንተም በነገርኸኝ መሠረት በቀጠሮው ቀን እንዳልመጣህ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ማኪማስ እንደ ተሰበሰቡ አየሁ፤
ያንጊዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎችን ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱም ሺህ በማኪማስና በቤቴል ተራራ ከሳኦል ጋር ነበሩ፤ አንዱም ሺህ በብንያም ገባዖን ከልጁ ከዮናታን ጋር ነበሩ፤ የቀረውንም ሕዝብ እያንዳንዱን ወደ ድንኳኑ አሰናበተ።
እግዚአብሔርም በዚያ ቀን እስራኤልን አዳነ፤ ውጊያውም በባሞት በኩል አለፈ። ከሳኦልም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ዐሥር ሺህ የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ውጊያውም በተራራማው በኤፍሬም ከተማ ሁሉ ተበታትኖ ነበር።
በሳኦልም ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፤ ሳኦልም ጽኑ ወይም ኀያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰበስብ ነበር።
ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ለጦርነት ሰበሰቡ፤ ራሳቸውም በይሁዳ በሰኮት ተሰበሰቡ፤ በሰኮትና በዓዜቃ መካከል በኤፌርሜም ሰፈሩ።
እግዚአብሔርም ፍልስጥኤማውያንን አዋረዳቸው፤ ዳግመኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስራኤል ድንበር አልወጡም፤ በሳሙኤልም ዘመን ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ነበረች።