Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 10:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ወደ አን​ጋይ ከተማ ይመ​ጣል፤ በመ​ጌ​ዶን በኩል ያል​ፋል፤ በማ​ክ​ማ​ስም ውስጥ ዕቃ​ውን ያኖ​ራል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ወደ ዐያት ይገባሉ፣ በሚግሮን ያልፋሉ፤ ጓዛቸውንም በማክማስ ያከማቻሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ወደ ዐያት ይገባሉ፤ በሚግሮን ያልፋሉ፤ ጓዛቸውንም በማክማስ ያከማቻሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 የጠላት ሠራዊት ወደ ዓይ ከተማ ደረሰ፤ በሚግሮንም በኩል ሲያልፉ ጓዛቸውን በሚክማስ አኖሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ወደ አንጋይ መጥቶአል፥ በመጌዶን በኩል አልፎአል፥ በማክማስም ውስጥ ዕቃውን አኑሮአል፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 10:28
12 Referencias Cruzadas  

ሳኦ​ልም በመ​ጌ​ዶን ባለው በሮ​ማኑ ዛፍ በታች በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ረው ሕዝብ ስድ​ስት መቶ የሚ​ያ​ህል ሰው ነበረ።


ያን​ጊ​ዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎ​ችን ከእ​ስ​ራ​ኤል መረጠ፤ ሁለ​ቱም ሺህ በማ​ኪ​ማ​ስና በቤ​ቴል ተራራ ከሳ​ኦል ጋር ነበሩ፤ አን​ዱም ሺህ በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ከልጁ ከዮ​ና​ታን ጋር ነበሩ፤ የቀ​ረ​ው​ንም ሕዝብ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ወደ ድን​ኳኑ አሰ​ና​በተ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ለመ​ዋ​ጋት ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሠላሳ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ስድ​ስት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ በባ​ሕ​ርም ዳር እን​ዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ወጥ​ተ​ውም ከቤ​ቶ​ሮን በአ​ዜብ በኩል በማ​ኪ​ማስ ሰፈሩ።


የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ከጌባ ጀምሮ በማ​ኬ​ማስ፥ በአ​ያል፥ በቤ​ቴ​ልና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥


ዳዊ​ትም ዕቃ​ውን በዕቃ ጠባ​ቂው እጅ አኖ​ረው፤ ወደ​ሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ሮጦ ሄደ፤ የወ​ን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ደኅ​ን​ነት ጠየቀ።


በዚ​ያም ቀን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በማ​ኪ​ማስ መቱ​አ​ቸው፤ ሕዝ​ቡም እጅግ ደከሙ።


አን​ደ​ኛዋ መን​ገድ በማ​ኪ​ማስ አን​ጻር በመ​ስዕ በኩል የም​ት​መጣ ናት፤ ሁለ​ተ​ኛ​ዋም መን​ገድ በገ​ባ​ዖን አን​ጻር በአ​ዜብ በኩል የም​ት​መጣ ነበ​ረች።


እነ​ር​ሱም ተመ​ል​ሰው ሄዱ፤ ቤተ ሰቡን፥ ገን​ዘ​ቡ​ንና ሀብ​ቱ​ንም ሁሉ፥ በፊ​ታ​ቸው አድ​ር​ገው ወሰዱ።


ኢያ​ሱም ከቤ​ቴል በም​ሥ​ራቅ በኩል በቤ​ት​አ​ዊን አጠ​ገብ ወዳ​ለ​ችው ወደ ጋይ ሰዎ​ችን ከኢ​ያ​ሪኮ ልኮ፥ “ውጡ፤ ጋይ​ንም ሰልሉ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ሰዎ​ቹም ወጡ፤ ጋይ​ንም ሰለሉ።


ከዚ​ያም ጥቂ​ቶች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ወደ ማኪ​ማስ መተ​ላ​ለ​ፊያ ወጡ።


ከይ​ሁዳ ወንድ ሰውን ሁሉ ያጠ​ፋል፤ ኀያ​ላ​ኑ​ንም ይጨ​ር​ሳል፤ ሰፈ​ሩም በሰ​ፊው ምድ​ርና በሀ​ገ​ሮ​ቻ​ቸው ሁሉ ይሞ​ላል፤” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ነውና።


ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios