Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 7:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አዋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ዳግ​መ​ኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስ​ራ​ኤል ድን​በር አል​ወ​ጡም፤ በሳ​ሙ​ኤ​ልም ዘመን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ነበ​ረች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በዚህ ሁኔታ ፍልስጥኤማውያን ድል ስለ ተመቱ፣ የእስራኤልን ምድር ዳግመኛ አልወረሩም። ሳሙኤል በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከብዳ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በዚህ ሁኔታ ፍልስጥኤማውያን ድል ስለተመቱ የእስራኤልን ምድር ዳግመኛ አልወረሩም። ሳሙኤል በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ የጌታ እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ነበረች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በዚህም ዐይነት ፍልስጥኤማውያን ድል ተመቱ። ሳሙኤል በኖረበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስለ ነበረ ፍልስጥኤማውያን ዳግመኛ ወደ እስራኤል ድንበር አልቀረቡም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ፍልስጥኤማውያንም ተዋረዱ፥ ዳግመኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስራኤል ድንበር አልወጡም፥ በሳሙኤል ዕድሜ ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ነበረች።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 7:13
12 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አርባ ዓመት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ልጁም ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ጀምሮ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ናዝ​ራዊ ይሆ​ና​ልና በራሱ ላይ ምላጭ አይ​ድ​ረ​ስ​በት፤ እር​ሱም እስ​ራ​ኤ​ልን ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ማዳን ይጀ​ም​ራል።”


ከሄ​ደ​ችም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ላይ መጣች፤ ታላቅ ሁከ​ትም ሆነ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሰዎች ታላ​ቁ​ንም ታና​ሹ​ንም መታ፤ የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ው​ንም በእ​ባጭ መታ​ቸው፤ የጌት ሰዎ​ችም የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን ምስል ሠሩ፥


ምድ​ያ​ምም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተዋ​ረዱ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ዳግ​መኛ አላ​ነ​ሡም፤ በጌ​ዴ​ዎ​ንም ዕድሜ ምድ​ሪቱ አርባ ዓመት ዐረ​ፈች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሩ​በ​ኣ​ልን፥ ባር​ቅ​ንም፥ ዮፍ​ታ​ሔ​ንም፥ ሳሙ​ኤ​ል​ንም ላከ፤ በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም ካሉት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ እጅ አዳ​ኑ​አ​ችሁ፤ ተዘ​ል​ላ​ች​ሁም ተቀ​መ​ጣ​ችሁ።


ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ አዋ​ረ​ዳ​ቸ​ውም፤ ዳዊ​ትም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ምር​ኮን ወሰደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios