1 ጴጥሮስ 2:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም እንኳ ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል በመልካም ሕይወት ኑሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር በሚጎበኝበት ቀን፥ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ እርሱን እንድያከብሩት በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ቀን አሕዛብ መልካም ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ በእነርሱ መካከል ስትኖሩ መልካም ጠባይ ይኑራችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን። |
ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!
አንቺን ይጥሉሻል፤ ልጆችሽንም ከአንቺ ጋር ይጥሉአቸዋል፤ ድንጋይንም በደንጋይ ላይ አይተዉልሽም፤ የይቅርታሽን ዘመን አላወቅሽምና።”
ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ቢጠሉአችሁ፥ ከሰው ለይተው ቢአሳድዱአችሁ፥ ቢሰድቡአችሁ፥ ክፉ ስምም ቢአወጡላችሁ ብፁዓን ናችሁ።
ስምዖንም፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ አሕዛብን ይቅር እንዳላቸውና ከውስጣቸውም ለስሙ ሕዝብን እንደ መረጠ ተናግሮአል።
ጳውሎስም በቀረበ ጊዜ ከኢየሩሳሌም የወረዱ አይሁድ ከብበውት ቆሙ፤ ሊረቱ በማይችሉበትም ብዙና ከባድ ክስ ከሰሱት።
ነገር ግን በዚህ ነገር በየስፍራው ሁሉ እንዲጣሉ በእኛ ዘንድ ታውቋልና የአንተን ዐሳብ ደግሞ ከአንተ እንሰማ ዘንድ እንወድዳለን።”
በቀን እንደሚሆን በጽድቅ ሥራ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር፥ በዝሙትና በመዳራትም አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን።
አሕዛብም እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፤ ይቅር ብሎአቸዋልና፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ መካከል እገዛልሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ።”
በልባቸው የደበቁትም ይገለጣል፤ ከዚህ በኋላ ያ የማያምነው ተመልሶ ይጸጸታል፤ በግንባሩም ወድቆ ለእግዚአብሔር ይሰግዳል፥ በእውነት እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለም ይናገራል።
በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን።
ምንም ክፉ ሥራ እንዳትሠሩ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ መልካም ነገር እንድታደርጉ ብቻ ነው እንጂ እኛ ደጎች ልንባል አይደለም፤ እኛም እንደ ተናቁ ሰዎች እንሆናለን።
እኛ ሁላችን ቀድሞ እንደ ሥጋችን ምኞት ኖርን፤ የሥጋችንንም ፈቃድና ያሰብነውን አደረግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥአንም ሁሉ የጥፋት ልጆች ሆንን።
ነገር ግን ምናልባት የመጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳልኖርም ቢሆን በወንጌል ሃይማኖት እየተጋደላችሁ በአንድ መንፈስና በአንድ አካል ጸንታችሁ እንደምትኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራችሁ ለክርስቶስ ትምህርት እንደሚገባ ይሁን።
አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ እውነትን ሁሉ፥ ቅንነትንም ሁሉ፥ ጽድቅንም ሁሉ፥ ንጽሕናንም ሁሉ፥ ፍቅርንና ስምምነትንም ሁሉ፥ በጎነትም ቢሆን፥ ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ አስቡ።
ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።
ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤