1 ነገሥት 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ኢዮርብዓም የእግዚአብሔርን ሰው፥ “አሁን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ፊት ለምን፤ እጄም ወደ እኔ ትመለስ ዘንድ ስለ እኔ ጸልይ” አለው፥ የእግዚአብሔርም ሰው እግዚአብሔርን ለመነ፤ የንጉሡም እጅ ወደ እርሱ ተመለሰች። እንደ ቀድሞም ሆነች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሡ የእግዚአብሔርን ሰው፣ “እጄ ወደ ቦታዋ እንድትመለስ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ለምንልኝ፤ ጸልይልኝም” አለው፤ ስለዚህም የእግዚአብሔር ሰው እግዚአብሔርን ለመነ፤ የንጉሡ እጅ ወደ ቦታዋ ተመለሰች፤ እንደ ቀድሞዋም ሆነች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ ኢዮርብዓም “እባክህ እጄን ያድንልኝ ዘንድ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ጸልይልኝ!” ሲል የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመነው። የእግዚአብሔርም ነቢይ ወደ ጌታ ጸልዮለት የንጉሡ እጅ ዳነች፤ እንደ ቀድሞም ሆነች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ኢዮርብዓም “እባክህ እጄን ያድንልኝ ዘንድ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልኝ!” ሲል የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመነው። የእግዚአብሔርም ነቢይ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮለት የንጉሡ እጅ ዳነች። እንደ ቀድሞም ሆነች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም የእግዚአብሔርን ሰው “አሁን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ፊት ለምን፤ እጄም ወደ እኔ ትመለስ ዘንድ ስለ እኔ ጸልይ፤” አለው። የእግዚአብሔርም ሰው እግዚአብሔርን ለመነ፤ የንጉሡም እጅ ወደ እርሱ ተመለሰች፤ እንደ ቀድሞም ሆነች። |
አሁን እንግዲህ እንደገና በዚህ ጊዜ ብቻ ኀጢአቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ” አላቸው።
ፈርዖንም፥ “ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በምድረ በዳ ትሠዉ ዘንድ እለቅቃችኋለሁ፤ ነገር ግን በጣም ርቃችሁ አትሂዱ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸልዩልኝ” አለ።
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፥ “ጓጕንቸሮቹን ከእኔ፥ ከሕዝቤም እንዲያርቅ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ ለእግዚአብሔርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝቡን እለቅቃለሁ” አላቸው።
እንግዲህ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ የአምላክ ነጐድጓድ፥ በረዶውም፥ እሳቱም ጸጥ ይላል፤ እኔም እለቅቃችኋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚህ አትቀመጡም” አላቸው።
ንጉሡም ሴዴቅያስ፥ “ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ስለ እኛ ጸልይ” ብሎ የሰሌምያን ልጅ ዮካልንና ካህኑን የማሴውን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ።
ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው፥ “በእግዚአብሔርና በአንተ ስለ ተናገርን በድለናል፤ እባቦችን ከእኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት። ሙሴም ስለ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን ኣያውቁምና ይቅር በላቸው” አለ፤ በልብሱም ላይ ዕጣ ተጣጣሉና ተካፈሉ።
በጕልበቱም ተንበርክኮ፥ “አቤቱ፥ ይህን ኀጢአት አትቍጠርባቸው” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ ሞተ፤ ሳውልም በእስጢፋኖስ ሞት ተባባሪ ነበር።
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።
ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፥ “ንጉሥ በመለመናችን በኀጢአታችን ሁሉ ላይ ይህን ክፋት ጨምረናልና እንዳንሞት ስለ ባሪያዎችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት።
ደግሞ መልካሙንና ቅኑን መንገድ አሳያችኋለሁ እንጂ ስለ እናንተ መጸለይንና እግዚአብሔርን ማገልገልን በመተው እርሱን እበድል ዘንድ እግዚአብሔር ይህን አያድርግብኝ።