Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 10:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አሁን እን​ግ​ዲህ እን​ደ​ገና በዚህ ጊዜ ብቻ ኀጢ​አ​ቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህ​ንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነ​ሣ​ልኝ ዘንድ ወደ አም​ላ​ካ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እንግዲህ አሁን አንድ ጊዜ ደግሞ ኀጢአቴን ይቅር በሉኝና ይህን ቀሣፊ መዓት እንዲያስወግድልኝ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑልኝ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 አሁን እንግዲህ አንድ ጊዜ ብቻ ኃጢአቴን ይቅር በሉኝ፥ ይህንን ሞት ከእኔ እንዲያነሣልኝ ብቻ ጌታ አምላካችሁን ለምኑልኝ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እንግዲህስ እነሆ፥ አንድ ጊዜ ብቻ በደሌን ይቅር እንድትሉኝ እለምናችኋለሁ፤ ይህን ከባድ ቅጣት ከእኔ እንዲያስወግድም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑልኝ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አሁን እንግዲህ በዚህ ጊዜ ብቻ ኃጢአቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑ አላቸው፤”

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 10:17
13 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም ኢዮ​ር​ብ​ዓም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው፥ “አሁን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት ለምን፤ እጄም ወደ እኔ ትመ​ለስ ዘንድ ስለ እኔ ጸልይ” አለው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመነ፤ የን​ጉ​ሡም እጅ ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች። እንደ ቀድ​ሞም ሆነች።


ከዚ​ህም በኋላ ሰዎቹ ይበሉ ዘንድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ የበ​ሰ​ለ​ው​ንም ቅጠል በሚ​በ​ሉ​በት ጊዜ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ በም​ን​ቸቱ ውስጥ መርዝ አለ” ብለው ጮኹ፤ ይበ​ሉም ዘንድ አል​ቻ​ሉም።


ፈር​ዖ​ንም፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በም​ድረ በዳ ትሠዉ ዘንድ እለ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነገር ግን በጣም ርቃ​ችሁ አት​ሂዱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸል​ዩ​ልኝ” አለ።


ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችም በአ​ንተ፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም፥ በሹ​ሞ​ች​ህም ሁሉ ላይ ይወ​ጣሉ።”


ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹን ከእኔ፥ ከሕ​ዝ​ቤም እን​ዲ​ያ​ርቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝ​ቡን እለ​ቅ​ቃ​ለሁ” አላ​ቸው።


ፈር​ዖ​ንም ልኮ ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠራ፤ “አሁ​ንም በደ​ልሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነን።


እን​ግ​ዲህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ የአ​ም​ላክ ነጐ​ድ​ጓድ፥ በረ​ዶ​ውም፥ እሳ​ቱም ጸጥ ይላል፤ እኔም እለ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከዚህ አት​ቀ​መ​ጡም” አላ​ቸው።


አቤቱ፥ በመ​ከ​ራዬ ጊዜ አሰ​ብ​ኹህ፤ በጥ​ቂት መከ​ራም ገሠ​ጽ​ኸኝ።


ሕዝ​ቡም ወደ ሙሴ መጥ​ተው፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በአ​ንተ ስለ ተና​ገ​ርን በድ​ለ​ናል፤ እባ​ቦ​ችን ከእኛ ያር​ቅ​ልን ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን” አሉት። ሙሴም ስለ ሕዝቡ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ።


ሲሞ​ንም መልሶ፥ “ካላ​ች​ሁት ሁሉ ምንም እን​ዳ​ይ​ደ​ር​ስ​ብኝ እና​ንተ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ኑ​ልኝ” አለ።


ወን​ድ​ሞች፥ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ስለ እኔ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ትተጉ ዘንድ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ፍቅር እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


እር​ሱም እን​ዲህ ካለ ሞት አዳ​ነን፤ ያድ​ነ​ን​ማል፤ አሁ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ድ​ነን እር​ሱን እን​ታ​መ​ና​ለን።


አሁ​ንም እባ​ክህ ኀጢ​ኣ​ቴን ይቅር በለኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እሰ​ግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመ​ለስ” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos