መዝሙር 82:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነርሱ ግን ምንም አያውቁም፤ አይገባቸውምም፤ በጨለማ ይመላለሳሉ፤ በዚህም ጊዜ የምድር መሠረትዋ እየተናወጠ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዕውቀትም ማስተዋልም የላቸውም፤ በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ፤ የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አያውቁም፥ አያስተውሉም፥ በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፥ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንድነት ተካክለው ተማክረዋልና፤ በአንተ ላይ ሤራ ቈረጡ፤ ቃል ኪዳንም አደረጉ፤ |
“እግዚአብሔር ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን? ሰዎች እንጀራን እንደሚበሉ ክፉ አድራጊዎች ሕዝቤን ይበዘብዛሉ፤ እነርሱም ወደ እኔ ወደ እግዚአብሔር አይጸልዩም።” ይላል።
እግዚአብሔር “ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን? ሰዎች እንጀራን እንደሚበሉ ክፉ አድራጊዎች ሕዝቤን ይበዘብዛሉ፤ እነርሱም ወደ እኔ ወደ እግዚአብሔር አይጸልዩም።” ይላል።
ጥበበኞች ሰዎች መነሻና መድረሻቸውን ያውቃሉ፤ ሞኞች ግን ይህን ሁሉ አያውቁም፤” ይሁን እንጂ ጥበበኛም ሆነ ሞኝ ሁለቱም የሚኖራቸው ዕድል አንድ ዐይነት መሆኑን ተረዳሁ።
ይህም የሠራዊት አምላክ የወይን ቦታ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፤ እርሱም የይሁዳ ሕዝብ ደስ የሚሰኝበት ተክል ነው። መልካም ሥራ እንዲሠሩ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ በዚህ ፈንታ ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ፤ ቅን ፍርድ ይሰጣሉ ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ እነርሱ ግን ፍርድን በማጓደላቸው የሕዝቡ ጩኸት በዛ።
ሕዝቡ እንዲህ ይላሉ፦ “ፍትሕ ከእኛ ርቆአል፤ ጽድቅም ወደ እኛ አይደርስም፤ ብርሃን እንዲበራልን እንፈልጋለን፤ ነገር ግን ሁሉም ጨለማ ነው፤ ስለዚህ በድቅድቅ ጨለማ እንመላለሳለን።
ከዚህም በኋላ እንዲህ አልኳቸው፦ “የእስራኤል ሕዝብ ልጆች መሪዎችና የእስራኤል ሕዝብ ገዢዎች! አድምጡ! ትክክለኛ ፍርድን ማወቅ ይገባችሁ አልነበረምን?
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።
ነገር ግን “ጌታ የራሱ የሆኑትን ያውቃል፤” እንዲሁም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት የማይነቃነቅ የእግዚአብሔር መሠረት ጸንቶ ይኖራል።