መዝሙር 65:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ የመረጥካቸውና በተቀደሰ አደባባይህ እንዲኖሩ ወደ ራስህ ያቀረብካቸው፥ ደስ ይበላቸው፤ እኛም ከቤትህ በሚገኘው መልካም ነገርና ከመቅደስህ በሚገኘው በረከት እንረካለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብፁዕ ነው፤ አንተ የመረጥኸው፣ ወደ ራስህ ያቀረብኸው፣ በአደባባይህም ያኖርኸው፤ ከተቀደሰው መቅደስህ፣ ከቤትህም በረከት እንረካለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዓመፃ ነገር በረታብን፥ መተላለፋችንንስ አንተ ይቅር ትላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድር ሁላ ለአንተ ትሰግዳለች፥ ለአንተም ትገዛለች፥ ለስምህም ትዘምራለች። |
ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በቀሪውም ሕዝቡ ላይ በደልን የማይቈጥር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረት ማድረግ ስለሚያስደስትህ ቊጣህ ለዘለዓለም የሚቈይ አይደለም።
በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ማመስገን ይገባናል፤ የምናመሰግነውም እናንተ በመንፈስ ቅዱስ በመቀደሳችሁና እውነትን በማመናችሁ እንድትድኑ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ስለ መረጣችሁ ነው።
ድል የሚነሣውን በአምላኬ ቤተ መቅደስ ዐምድ አደርገዋለሁ፤ ከዚያም ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም በእርሱ ላይ እጽፋለሁ፤ ይህችም ከተማ ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደው አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ናት፤ የእኔንም አዲስ ስም በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።