Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 17:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እኔ በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ በምነቃበት ጊዜም የአንተን አምሳያ በማየቴ እደሰታለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ስነቃም ክብርህን አይቼ እረካለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፥ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አቤቱ፥ ከተ​ግ​ሣ​ጽህ፥ ከመ​ዓ​ት​ህም መን​ፈስ እስ​ት​ን​ፋስ የተ​ነሣ፥ የው​ኆች ምን​ጮች ታዩ፥ የዓ​ለም መሠ​ረ​ቶ​ችም ተገ​ለጡ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 17:15
23 Referencias Cruzadas  

ሰውም እንዲሁ ከሞተ በኋላ አይመለስም፤ ሰማይ እስከሚያልፍ ድረስ አይነቃም፤ ከእንቅልፉም አይነሣም።


እግዚአብሔር ጻድቅ ስለ ሆነ የጽድቅን ሥራ ይወዳል፤ ትክክለኛ ሥራ የሚሠራ ሰው ሁሉ ፊቱን ያያል።


ሕግህ ዘለዓለማዊ ሀብቴ ነው፤ የልቤም ደስታ እርሱ ነው።


የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ፊት ሙሉ ደስታ፥ በቀኝህም የዘለዓለም እርካታ ይገኛል።


እነዚህ እንደ በጎች እንዲሞቱና እንዲቀበሩ ይደረጋሉ፤ እረኛ በጎችን እንደሚመራ ሞትም እነዚህን ወደ መቃብር ይመራል፤ ትክክለኞች ሰዎች በማለዳ በመቃብራቸው ላይ ይመላለሳሉ፤ ሥጋቸውም በመቃብር ውስጥ ይበሰብሳል፤ የሙታን ዓለምም መኖሪያቸው ይሆናል። ደጋግ ሰዎችም በማለዳ ተነሥተው በእነርሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ።


እኔ ግን በታላቅ ምሕረትህ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ ወደ ቤተ መቅደስህ በአክብሮት እሰግዳለሁ።


አንተ የመረጥካቸውና በተቀደሰ አደባባይህ እንዲኖሩ ወደ ራስህ ያቀረብካቸው፥ ደስ ይበላቸው፤ እኛም ከቤትህ በሚገኘው መልካም ነገርና ከመቅደስህ በሚገኘው በረከት እንረካለን።


ሙታንህ ተነሥተው ሕያዋን ይሆናሉ፤ እናንተ በመቃብር ውስጥ የምትኖሩ፥ ተነሥታችሁ የደስታ መዝሙር ዘምሩ! አንጸባራቂው ጠል ምድርን እንደሚያድስ እግዚአብሔርም ከሞቱ ብዙ ጊዜ የሆናቸውን ተነሥተው በሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋል።


ስለዚህም በዚያን ጊዜ ሕዝቡ ‘ተኝተን ስንነቃ ታደስን’ ይላሉ።


ስለዚህም እኔ ከእርሱ ጋር ቃል ለቃል በግልጥ እነጋገራለሁ እንጂ ስውር በሆነ አነጋገር አልናገረውም፤ የእኔን የእግዚአብሔርን መልክ ያያል፤ ታዲያ፥ እናንተ በአገልጋዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ እንዴት ደፈራችሁ?”


ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ስለሚጠግቡ የተባረኩ ናቸው።


እኛ ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት ሆነን በመስታዋት እንደሚታይ ዐይነት የጌታን ክብር እናንጸባርቃለን፤ እኛም መንፈስ የሆነውን የጌታን መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።


እርሱ ይህን የተዋረደውን ሰውነታችንን በመለወጥ የእርሱን ክቡር ሰውነት እንዲመስል ያደርገዋል፤ ይህንንም የሚያደርገው ሁሉን በሥልጣኑ ሥር ለማድረግ በሚያስችለው ኀይል ነው።


እርሱን ማምለክ መልካም መስሎ ካልታያችሁ ግን የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በነበሩበት ጊዜ ያመልኩአቸው የነበሩትን ወይም አሁን በምድራቸው የምትኖሩባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደሆን የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ፤ እኔና ቤተሰቤ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።”


የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላትና በጉ መብራትዋ ስለ ሆነ ከተማይቱ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጋትም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos