Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 36:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በቤትህ የተትረፈረፈውን ምግብ ይጋበዛሉ፤ አስደሳች ከሆነ ወንዝህም ታጠጣቸዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከቤትህ ሲሳይ ይመገባሉ፤ ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን እንዴት አበዛህ! የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 መዓ​ትን ተዋት፤ ቍጣ​ንም ጣላት፥ እን​ዳ​ት​በ​ድ​ልም አት​ቅና።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 36:8
19 Referencias Cruzadas  

የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ፊት ሙሉ ደስታ፥ በቀኝህም የዘለዓለም እርካታ ይገኛል።


አንተ የመረጥካቸውና በተቀደሰ አደባባይህ እንዲኖሩ ወደ ራስህ ያቀረብካቸው፥ ደስ ይበላቸው፤ እኛም ከቤትህ በሚገኘው መልካም ነገርና ከመቅደስህ በሚገኘው በረከት እንረካለን።


እኔ ሁልጊዜ እመራችኋለሁ፤ በድርቅም ቦታ ፍላጎታችሁን አረካለሁ፤ አጥንታችሁንም አጠነክራለሁ፤ ውሃ እንደሚጠጣ የአትክልት ቦታና ደርቆ እንደማያውቅ ምንጭ ትሆናላችሁ።


የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል።


ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር በደስታ እዘምርልሃለሁ።


ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ስለሚጠግቡ የተባረኩ ናቸው።


ጅረቶችዋ የልዑል እግዚአብሔርን ቅዱስ ማደሪያ፥ የአምላክን ከተማ የሚያስደስቱ አንዲት ወንዝ አለች።


እግዚአብሔር በምድረ በዳ በመራቸው ጊዜ ውሃ አልጠማቸውም፤ ይልቁንስ ውሃ ከአለት እንዲፈልቅላቸው አደረገ። አለቱን ከፍሎ ውሃ አጐረፈላቸው።


የወይራ ዘይት እንደ ጐርፍ ሲወርድ፥ ማርና ወተት እንደ ጅረት ውሃ ሲፈስ ሳያይ ይሞታል።


የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን ኢየሱስ ቆመና ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “ውሃ የጠማው ቢኖር ወደ እኔ መጥቶ ይጠጣ፤


ለተመረጡት ሕዝቤ ውሃን ለመስጠት ወንዞች በበረሓ ጅረቶች በምድረ በዳ እንዲፈስሱ ባደረግሁ ጊዜ የምድር አራዊት እንኳ ሳይቀሩ ያከብሩኛል፤ ቀበሮዎችና ሰጎኖችም ያመሰግኑኛል።


እኔ በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ በምነቃበት ጊዜም የአንተን አምሳያ በማየቴ እደሰታለሁ።


እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ! እነሆ ወደ አትክልት ቦታዬ ገባሁ፤ ከርቤዬንና የሽቶ አበባዎቼን ለቀምኩ፤ የማር ሰፈፌን ከወለላው ጋር ተመገብኩ፤ የወይን ጠጄንና ወተቴንም ጠጣሁ። ወዳጆቼ ሆይ! በፍቅር እስክትረኩ ድረስ ብሉ፥ ጠጡ።


የምድሪቱም መልካምነትና ውበት ምንኛ አስደናቂ ይሆናል! በእርስዋ የሚገኘው እህልና የወይን ጠጅ ወጣት ወንዶችና ሴቶችን ያለመልማቸዋል።


የዐይን ብሌን በጥንቃቄ የሚጠበቀውን ያኽል ጠብቀኝ፤ በጥበቃህ ውስጥ ሰውረኝ።


ከሚያሤሩባቸው ሰዎች በመኖሪያህ ጥላ ሥር ትደብቃቸዋለህ፤ ከመርዘኛ አንደበትም በከለላህ ትጠብቃቸዋለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios