ከችግሬ ሁሉ አድነኸኛል፤ የጠላቶቼንም ውድቀት አየሁ።
ከመከራ ሁሉ ታድጎኛልና፤ ዐይኔም የጠላቶቼን ውድቀት ለማየት በቅቷል።
ክፋትን ወደ ጠላቶቼ ይመልሳታል፥ በእውነትህም አጥፋቸው።
እነሆ፥ ኮብልዬ በራቅሁ፥ በምድረ በዳም በኖርሁ፤
እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”
ዳዊትም ለሬካብና ለወንድሙ ለበዓና እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ከአደጋ ሁሉ ባዳነኝ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ!
በእግዚአብሔር ያለው እምነት እጅግ የጸና ስለ ሆነ ከቶ አይፈራም፤ በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።
እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ሆኖ ስለሚረዳኝ፥ የጠላቶቼን ውድቀት አያለሁ።
ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ግለጥልኝ፤ ጠላቶቼን አጥፋቸው፤ እኔ አገልጋይህ ስለ ሆንኩ ጥቃት የሚያደርሱብኝን ሁሉ ደምስሳቸው።
ጻድቅ ብዙ መከራ ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ ያድነዋል።
ይህ ድኻ ሰው ተጣራ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ከችግሩም ሁሉ አዳነው።
ተስፋህን በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፤ ትእዛዙንም ፈጽም፤ እርሱም ምድርን በማውረስ ያከብርሃል፤ ክፉዎች ሲወገዱም ታያለህ።
አምላኬ በዘለዓለማዊ ፍቅሩ በፊቴ ይሄዳል፤ ጌታዬ፥ ጠላቶቼን በንቀት ዐይን እንድመለከታቸው ያደርገኛል።
ክፉዎች ሲቀጡ በዐይንህ ታያለህ።
የጠላቶቼን መሸነፍ አየሁ፤ የአስጨናቂዎቼንም ውድቀት ሰማሁ።
ጌታ ከማንኛውም ክፉ ነገር ያድነኛል፤ በሰማይ ላለው መንግሥቱም ያበቃኛል፤ ለእርሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን! አሜን።
ዛሬ እኔ የአንተን ሕይወት እንዳከበርኩ፥ እግዚአብሔር እኔንም እንደዚሁ ከመከራ በማውጣት ይጠብቀኝ!”